Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet
query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
1
300
passage
stringlengths
95
13.7k
category
class label
6 classes
link
stringlengths
28
740
source_dataset
stringclasses
4 values
cb1046254be35c0da1666fb012884928
b080930c1c35070fe71498a332442fd6
ኮቪድ-19 በት/ቤቶች ላይ የፈጠረው ጫና
በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በማስገደዱ ዓለማችን በህፃናትትምህርት ላይ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚዘልቅ የከበደ አደጋ ተደቅኖበታል ሲሉ የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ አሳሰቡ።ዋና ፀኃፊው ይህን ያሳሰቡት "መፃኢ ተስፋችንን እንታደግ" በሚል ርዕስ የመንግሥታቱ ድርጅት የጀመረውን አዲስ ዘመቻ ትናንት ባስተዋወቁበት ንግግራቸው ነው።የዘመቻው ዓላማ በድህረ ኮቪድ-19 መደበኛ ትምህርትን መመለስና ማጠናከር ላይ ትኩረት መስጠት መሆኑ ተገልጿል።እኤአ ሃምሌ አጋማሽ ድረስ በ106 ሃገሮች ከ1ቢሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸውና 40ሺህ ህፃናት ደግሞ ከመዋዕለ ህጻናት ውጪ ሆነዋል ብለዋል።ወረርሽኙን ከተቆጣጠርን በኋላ ቅድሚያ ትኩረታችን ህፃናትን ወደትምህርት ገበታቸው መመለስ መሆን ይኖርበታል ሲሉ አሳስበው በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ ልጃገረዶች፣ ስደተኞችና ተፈናቃዮች የተለየ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
4ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/generational-catastrophe-possible-as-pandemic-creates-education-crisis-8-4-2020/5530199.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
a95ba189bc4a079346e5fe9c97b4661c
97d0dbd8ea8cf7287934d354be5a6ed6
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከጃፓንና ደቡብ ኮሪያ መሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በሚቀጥለው ሳምንት ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ እና ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር ሊወያዩ ነው።መሪዎቹ የሚያካሂዱት የሶስትዮሽ ውይይይት በፈረንጆቹ  የፊታችን ታህሳስ 24 ቀን በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቸንግዱ ከተማ የሚያካሄድ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ከሶስትዮሽ ውይይቱ በፊትም ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሀገራቱ መሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የተናጠል ውይይት የሚያድርጉ መሆኑ ተመላክቷል።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥መሪዎቹ በሶስትዮሽ ውይይታቸው  በተለያዩ ቀጠናዊና እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ መሆኑን አስታውቋልበተለይም በሰሜን ኮሪየ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ዙሪያ በጥልቀት የሚመክሩ መሆኑ ነው የተገለጸው።በቅርቡ ሩሲያ እና ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ኮሪያ ላይ ከጣላቸው ማዕቀቦች ውስጥ የተወሰኑት እንዲነሱ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል።ይህም ሰሜን ኮሪያ በኒውክሌር የጦር መሳሪያ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን ድርድር እንደ አዲስ በመጀመር አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያበረታታ መሆኑ ተገልጿል።አሜሪካ በበኩሏ በሩሲያ እና ቻይና የቀረበው ረቂቅ ሃሳብ በትክክለኛው ጊዜ ያልቀረበ ከመሆኑ ባሻር የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ስትል አጣጥላዋለች።ምንጭ፦  ሲ ጂ ቲ ኤን
4ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9a%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%ba-%e1%8c%82%e1%8a%95%e1%8d%92%e1%8a%95%e1%8c%8d-%e1%8a%a8%e1%8c%83%e1%8d%93%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%8a%ae/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
39dba64ac8cfa971ce8fcb2e4a4941df
222a07c9df164055eeffc35d004c33b4
የከፍተኛ ሊግ ወሳኝ ጨዋታዎች እና ሌሎች መረጃዎች
የምድብ ሐ ሁለት ጨዋታዎች አይከናወኑምየከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ 20ኛ ሳምንት አራት ጨዋታዎች ነገ ሲደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ግን ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገራቸውን የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አስታውቋል። በነቀምት ከተማው ተጫዋች ወንድወሰን ዮሐንስ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ነቀምት ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የማይኖር በመሆኑ የመሪው ሀዲያ ሆሳዕና እና ከምባታ ሺንሺቾ ጨዋታ መራዘሙን አቶ ኢብራሂም አህመድ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ” ሊጉ ውበቱን ጠብቆ እንዲጓዝ የሁለቱ ጨዋታን በይደር አቆይተነዋል። ሌሎቹ ጨዋታዎች ግን ይደረጋሉ፤ በተመረጡ ጨዋታዎች ላይም ተጨማሪ ተቆጣጣሪዎች ተልከዋል። ” ያሉት አቶ ኢብራሂም በነቀምቱ ተጫዋች ወንድወሰን ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘንም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስም ገልፀዋል።ሁለት ተፎካካሪዎች የቀሩበት የምድብ ሀ ትንቅንቅበምድብ ሀ ባለፈው ሳምንት ደሴ ከተማ ተስተካካይ ጨዋታውን ከወሎ ኮምቦልቻ ጋር አድርጎ አቻ በመለያየቱ ከምድቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማለፍ የሚደረገው ፉክክር በሰበታ ከተማ እና ለገጣፎ ለገዳዲ መካከል ሆኗል። በ20ኛው ሳምንት ሁለቱም ቡድኖች ጠንካራ ጨዋታ የሚጠብቃቸው ሲሆን ሰበታ ከተማ ከ ደሴ ከተማ፤ ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይጫወታሉ።የአራት ነጥብ ልዩነት ይዞ ምድቡን እየመራ የሚገኘው ሰበታ ከተማ አንድ እግሩን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የማስገባት አላማን አንግቦ ደሴ ከተማን በሜዳው ያስተናግዳል። ሰበታ ይህን ጨዋታ አሸንፎ ለገጣፎ የሚሸነፍ ከሆነም ከ2003 በኋላ ዳግም ወደ ሊጉ መመለሱን የሚያረጋግጥ ይሆናል።በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እየሰለጠነ የሚገኘው ሰበታ ከተማ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ሽንፈት ያላስተናገደ ብቸኛው የከፍተኛ ሊግ ቡድን ሲሆን ደሴ በአንፃሩ በሁለተኛው ዙር ከየትኛውም ቡድን በተሻለ ከፍተኛ ማንሰራራት አሳይቶ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።በጨዋታው ዙርያ የሰበታ ከተማው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ለሶከር ኢትዮጵያ ይህን ብለዋል። ” ጨዋታው ከበድ ይላል። ምክንያቱም ደሴ ከተማ በሁለተኛው ውድድር አጋማሽ ተጠናክሮ የቀረበ ቡድን ነው። ሆኖም ቡድኔ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሥነ ልቦናም ሆነ በአካል ብቃት እንዲሁም በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል። በልምምድ ሜዳ ሳለን ከንቲባው ሜዳ ድረስ በመምጣት ተጫዋቾቼንም ሆነ የአሰልጣኙን አባላት አበረታተዋል። አሁን ደጋፊው ላይ ትልቅ መነቃቃት ተፈጥሯል። ይህም ለኛ ሌላ ኃይል ነው። በሜዳችን ያለመሸነፍ ጉዛችንን አስጠብቀን እንጓዛለን። ” ብለዋል።ሁለቱ ቡድኖች በመጀመርያው ዙር ደሴ ላይ ባደረጉት ጨዋታ ሰበታ 2-1 አሸንፎ ተመልሷል።ለገጣፎ ለገዳዲ የሰበታን ነጥብ መጣል ተስፋ በማድረግ ከሜዳው ኢትዮ ኤሌክትሪክን ይገጥማል። በወጣቱ አሰልጣኝ ዳዊት የሚመራው ለገጣፎ በአራት ነጥብ የራቀው ሰበታ ከተማን በ21ኛ ሳምንት በሜዳው የሚያስተናግድ እንደመሆኑ ከዚህ ጨዋታ ሙሉ ሦስት ነጥብ ማግኘት ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመግባት ለሚያደርገው ጉዞ ስንቅ ይሆነዋል።የለገጣፎው አሰልጣኝ ዳዊት ሐብታሙ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ተጋጣሚያቸው ተቀራራቢ አጨዋወት ያለው መሆኑ እንደሚያመቻቸው ተናግረዋል። ” ተጋጣሚያችን ኳስን መሰረት አድርጎ የሚጫወት ቡድን ነው። በመጀመሪያው ዙር ባደረግነው ጨዋታ በደንብ አይተናቸዋል። አጨዋወታቸው ከእኛ ጋር ተቀራራቢ እንደመሆኑ የስፖርት ቤተሰብ ጥሩ ጨዋታ የሚያይ ይመስለኛል። ቡድናችን አሁን ላይ አንድ ተጫዋች በቅጣት ከማጣቱ ውጪ ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ይህን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ የምናደርገውን የትንቅንቅ አጠናክረን እንቀጥላለን። ተጫዋቾቼም ይህን ያደርጉታል። ” ብለዋል።በመጀመሪያው ዙር መርሀ ግብር ለገጣፎ ላይ ባደረጉት ጨዋታ ለገጣፎ ለገዳዲ 1-0 ማሸነፉ ይታወሳል።የሜዳ ለውጥ መድን ሜዳ ላይ ጨዋታውን ሲከናውን የቆየው ኢኮስኮ በዚህ ሳምንት የሜዳ ለውጥ አድርጓል። ምክንያት ተብሎ የቀረበው የኢትዮጵያ መድን ሜዳውን ለጤና ቡድን በመሰጠቱ ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያደርግ የቡድን መሪው ሙሉጌታ አሰፋ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ እና ቡራዩ ከተማ ጨዋታም በተመሳሳይ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በ4:00 ይካሄዳል።የሳምንቱ ጨዋታዎች (20ኛ ሳምንት)ምድብ ሀ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2011አቃቂ ቃሊቲ (9:00) ቡራዩ ከተማ ፌዴራል ፖሊስ (9:00) ወልዲያ አክሱም ከተማ (9:00) ወሎ ኮምበልቻ አውስኮድ (9:00) ገላን ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (9:00) ለገጣፎ ለገዳዲ ሰበታ ከተማ (9:00) ደሴ ከተማምድብ ለ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2011ሀላባ ከተማ (9:00) ሶዶ ከተማ ናሽናል ሴሜንት (9:00) የካ ክ/ከተማ ድሬዳዎ ፖሊስ (9:00) ነገሌ አርሲ ኢኮስኮ (9:00) አዲስ አበባ ከተማ ዲላ ከተማ (9:00) ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾ (9:00) ወልቂጤ ከተማምድብ ሐ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2011ቡታጅራ ከተማ (9:00) ቤንች ማጂ ቡና ነገሌ ቦረና (9:00) ጅማ አባቡና ሻሸመኔ ከተማ (9:00) ስልጤ ወራቤ ካፋ ቡና (9:00) ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ
2ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/48814
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1b499a6548c059ea4b3aac1273f51116
461eb83b299aa3d15d343b6005f22663
በኦሮሚያ ክልል ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአምስት ሺሕ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ለገሱ
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ ከመኖሪያ ቤታቸው ለተፈናቀሉና በአብያተ ክርስቲያናትና በሌሎች ሥፍራዎች ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች፣ በአዲስ አበባ ሰብዓዊ ዕርዳታ እየተሰበሰበ ነው፡፡ ከአምስት ሺሕ በላይ ሰዎች ዕርዳታ መለገሳቸው ታውቋል፡፡ከረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ የተጀመረው ተቃውሞ ወደ ግጭት ተለውጦ በተፈጸሙ ጥቃቶች 78 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ በርካቶች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ ሥፍራዎች ተጠልለዋል፡፡ በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለእነዚህ ወገኖች እየተሰበሰበ በሚገኘው ዕርዳታ ከልጅ እስከ አዋቂ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዕርዳታቸውን እየለገሱ መሆናቸውን፣ እስከ ዓርብ ጥቅምት 21 ቀን 2012 በተደረገው ዕርዳታም ከአምስት ሺሕ በላይ ግለሰቦች ደረቅ ምግቦች፣ ዘይት፣ አልባሳት፣ ውኃና የቤት ቁሳቁሶች ማበርከታቸውን የዕርዳታ አስተባባሪዎች አስረድተዋል፡፡ ሰብዓዊ ዕርዳታውን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚያስተባብሩት አንዱ አቶ መሐመድ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱት ችግሮች እርስ በርስ አለመደማመጥ፣ በዕርጋታ አለመነጋገርና የጥሞና መጉደል የፈጠረው መሆኑንና ይህም በርካታ ንፁኃን ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉና ዕርዳታ እንዲሹ ምክንያት ሆኗል፡፡ አንድ ሰው ሠርቶ ብዙ ቤተሰቡን በሚያስተዳድርበት፣ ታላላቆች ታናናሾቻቸውን በሚንከባከቡበት የኢትዮጵያ የአኗኗር ዘይቤ እንዲህ ዓይነቱ ችግር ሲከሰት ጉዳቱ እንደሚከብድ ያስታወሱት አቶ መሐመድ፣ ለእነዚህ ወገኖች ሰብዓዊ ዕርዳታውን አጠናክሮ ቶሎ መድረሱ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ በግጭት ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ሲፈናቀሉ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንና የመንቀሳቀስ ችግር ያለባቸው እንደሚጎዱና ለእነዚህ ወገኖች ሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረግ፣ አለሁ ማለትና ከጎን መቆም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ቅድሚያ ለሰብዓዊነት በሚል ዕርዳታዎችን ሲያሰባስቡ እንደነበር፣ አሁን ‹‹ኬር ኤንድ ሼር›› በሚል በማኅበራዊ የትስስር ገጾች ዕርዳታ ከሚያደርግ ቡድን ጋር ተባብረው እየሠሩ መሆኑን፣ በዚህም አልሚ ምግቦችንና የሕክምና ቁሳቁስን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. የተጀመረው ሰብዓዊ ዕርዳታ የማሰባሰብ ሥራ እስከ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን ድረስ የሚዘልቅ መሆኑንና አርቲስቶች፣ የጉዞ ዓድዋ ተጓዦች፣ የእምነት አባቶችና ሌሎችም በጎ ፈቃደኞች በዓይነት ብቻ የሚሰጠውን ዕርዳታ እያስተባበሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ በሥፍራው ሲያስተባብር የነበረው አቶ ያሬድ ሹመቴ ዕርዳታ የማሰባሰቡን ሥራ እነሱ ሲያከናውኑ፣ ዕርዳታውን ተፈናቃዮች ወዳሉባቸው አካባቢዎች በመውሰድ የሚተባበሩት ቀይ መስቀል ማኅበርና ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መሆናቸውን አስረድቷል፡፡ እስካሁን ወደ አርሲ ዶዶላ ከሕፃናት እስከ አዋቂ ሊያገለግሉ የሚችሉ ምግብና አልባሳት በአንድ መኪና ተጭነው የተላኩ ሲሆን፣ በቀጣይ ችግሩ ባሉባቸው አካባቢዎች ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን አክሏል፡፡ ድሬዳዋ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ ሮቤ፣ አርሲ ዶዶላና ኮፈሌ በአስቸኳይ የሚላኩባቸው ቦታዎች እንደሆኑና ከዚህ በኋላም በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እንደሚላክ ጠቁመዋል፡፡ ኅብረተሰቡ እስከ ቀነ ገደቡ በዓይነት ብቻ ዕርዳታ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እስከ ሐሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ከለጋሾች ከስምንት እስከ አሥር ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የዕርዳታ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን፣ አስተባባሪዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
5ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/17188
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3626bd3990fdb3859df7fe8b210253f3
87e85991a86d359f5e1ff57c187d8e35
​”የተሰጠኝን ሚና በትጋት መወጣት ነው የምፈልገው” ሱሌይማን ሰሚድ
ሱሌማን ሰሚድ ይባላል። ለአዳማ ከተማ በቀኝ መስመር ተከላካይነት አመዛኙን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በመጀመርያ ተሰላፊነት እየተጫወተ ይገኛል። ከተለመደ ቦታው ውጪ እየተጫወተ የሚገኘው የአዳማው 24 ቁጥር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያሳየ ይገኛል። ሱሌይማን በእግርኳስ ህይወቱ፣ በሚና ለውጡ እና በወደፊት እቅዶቹ ዙርያ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ። የሱሌይማን ትውልድ እና እድገት በቅርብ አመታት ኮከቦችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ እያበረከተች በምትገኘው አሶሳ ከተማ ነው። የወጣቱ የእግርኳስ ህይወት የተጀመረውም በዚሁ ከተማ መንደሮች በመጫወት ነው። ” ከመኖርያ ቤቴ አካባቢ 50 ሜትር ርቆ ትልቅ ስታድየም አለ። ከትምህርት ቤት ስመለስ የእኔ ታላላቆች ኳስ ሲጫወቱ ከጎል ጀርባ በመሆን የሚጫወቱበትን ኳስ እያቀበልኩ ሰው ሲጎድልባቸው ደግሞ አብሬ እየተጫወትኩ የእግርኳስ ተጨዋች የመሆን ፍላጎቴ እየጨመረ መጣ። በኋላም ለትምህርት ቤት ውድድር መጫወት ጀምሬ ባለበት አጋጣሚ በፍቃዱ የተባለ አሰልጣኝ የሚመራው ሲት ቦይስ የሚባል ፕሮጀክት ነበር። አሰልጣኙ የማደርገውን ጥሩ እንቅስቃሴ በመመልከት ‘ ና እዚህ ፕሮጀክት ስራ። እኔ እፈልግሀለው። ‘ ብሎ ሲጠራኝ በሙሉ ፍቃደኝነት ወደ ፕሮጀክት በመቀላቀል እግርኳስን ህይወቴን በአሰልጣኝ የመሰልጠን ጅማሮዬን አደረኩ” ይላል። ሱሌማን በዚህ ፕሮጀክት በቆየባቸው የሁለት አመታት ብዙ የእግርኳስ መሰረታዊ ስልጠናዎችን እንዳገኘ ይገልፃል። በትልቅ ደረጃ እግርኳስ ተጨዋች ለመሆን የሚያስችለውን ህልሙን ሊያሳካ የሚችልበት መንገድ የተጠረገለት ግን በ2006 ሻሸመኔ ላይ በተደረገ ውድድር ነበር።” በ2006 ሻሸመኔ ከተማ ላይ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የፕሮጀክት ምዘና ውድድር ላይ አሶሳን በመወከል ተሳትፌ ባሳየሁት ጥሩ እንቅስቃሴ ተመርጬ ከቤተሰብ ከትውልድ ስፍራዬ ርቄ ወደ አአ በመምጣት የኢትዮዽያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን ተቀላቀልኩ። ለሦስት ተከታታይ አመታት በጣም ጠቃሚ የሆኑ ስልጠናዎችን አግኝቻለሁ። አሁን ላለው የእግርኳስ ህይወቴ መሰረት የጣልኩበት ቆይታም አድርጌያለው። በአካዳሚ ቆይታዬ አበበ በቂላ ስታድየም ላይ በአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሚዘጋጀው የተስፋ ቡድኖች ጨዋታዎች ላይም ተሰላፊ ነበርኩ። ” እውነት ለመናገር በአካዳሚ ውስጥ ገብቶ እግርኳስን መሰልጠን ብዙ ጠቀሜታ ቢኖረውም ዋናው ነገር ከቤተሰብ ከትውልድ መንደርህ ተለይተህ አካዳሚ ስትገባ የሆነ አላማ እንዳለህ ታስባለህ። ይህን አላማ ለማሳካት ደግሞ አሰልጣኞች ከሚሰጡኝ ስልጠና ባሻገር በግል የተለያዩ ልምምዶችን ጠንክረህ እንድሰራ አድርጎኛል። ስለዚህ አካዳሚ ገብቼ ያገኘሁት ጠቀሜታ በአላማ እንድትኖር ለአላማ እንድትሰራ ፣ ፕሮፌሽናል የመሆን ህልም እንዲኖርህ አንተን ብቁ ሊያደርግ የሚያስችል የስልጠና ማዕከል ነው ” ተስፈኛው ወጣት በአካዳሚ በነበረው ቆይታ ቡድኑ በተስፋ ውድድር ላይ በሚያሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ጎልቶ መውጣት ችሏል። በአካዳሚው ለነበረው ቆይታ እና ለነበረው ጥሩ ጊዜ እንዲሁም ድጋፍ ላደረጉለት አካላት በሙሉ ምስጋናውን ያቀርባል። የሱሌይማን ቀጣይ ማረፍያ እና የመጀመርያ ክለቡ አዳማ ከተማ ነው። ተጫዋቹ በ2008 ክረምት አካዳሚን ለቆ በአሸናፊ በቀለ የሚሰለጥነውን ቡድን የተቀላቀለበትን መንገድ እንዲህ ያስረዳል። ” በአአ የተስፋ ቡድኖች ጨዋታ ላይ በነበረኝ አቋም ከሁለትም ሦስት ቡድን ፈልገውኝ ነበር። ሆኖም እኔ የመጀመርያ ምርጫዬ አዳማ ከተማ ስለነበር ከ2009 ጀምሮ በአዳማ ከተማ በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ስብስብ ውስጥ ተካትቼ በመስራት የመጀመርያ ጨዋታዬንም በአአ ሲቲ ካፕ ላይ የአዳማ ማልያ በመልበስ መጫወት ጀመርኩ። በመቀጠል በፕሪምየር ሊጉ አንደኛ ዙር ላይ ሙሉ ለሙሉ የመጫወት እድል አላገኘሁም ነበር። በኋላ በሁለተኛው ዙር ላይ አልፎ አልፎ ቢሆንም ተቀይሮ በመግባት የመጫወት እድል አግኝቻለሁ። የበለጠ ግን ዘንድሮ በአአ ሲቲ ካፕ ላይ ባሳየሁት መልካም እንቅስቃሴ በፕሪምየር ሊጉ ከ10 ጨዋታ በ8ቱ የቋሚ ተሰላፊነት እድል አግኝቼ በመጫወት ላይ እገኛለው። ” ሱሌይማን ከተወለደበት መንደር በመውጣት የኢትዮጵያ ኮከብ የሆነው ሳላዲን ሰዒድን ምሳሌ ያደርጋል። የእርሱን ዱካ ተከትሎ የሀገሪቱ ምርጥ ተጫዋች መሆንም ይፈልጋል። በተስፋ ውድድር ላይ በአካዳሚ ማልያ ሲያደርገው የነበረው እንቅስቃሴም የሳላዲንን ፈለግ ተከትሎ ምርጥ አጥቂ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። ሆኖም አዳማ ከተማን ከተቀላቀለ ወዲህ በቀኝ መስመር ተከላካይነት እየተሰለፈ ይገኛል። ሱሌይማን ፍላጎቱ በአጥቂነት የመጫወት ቢሆንም በሚሰጠው ሚና ለመጫወት ዝግጁ እንደሆነ ይገልፃል። ” በአካዳሚ በነበረኝ ቆይታ የአጥቂ መስመር ተጨዋች ነበርኩ። ሆኖም ግን በአሁኑ ሰአት የተከላካይነት ስፍራ እንድጫወት ተደርጓል። ወጣት እንደመሆኔ መጠን ምንም እንኳን እግርኳስ መጫወት ስጀምር አጥቂ የመሆን ትልቅ ፍላጎት ቢኖረኝም ስራ እስከሆነ ድረስ አሰልጣኞች የሚሰጡኝ ሚና ሁሉ በትጋት በሚገባ መወጣት አለብኝ። ይህን ስታደርግ ደግሞ የፕሮፌሽናልነት አዕምሮ እንዲኖርህ ያደርገሀል።” በአዳማ ከተማ ዘንድሮ በ8 ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈው ሱሌይማን ቡድኑ በተጫዋች ስብስብ ጠንካራ እንደሆነ ገልጾ ካለው የነጥብ መቀራረብ አንፃር ካለፉት አመታት የተሻለ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ለማጠናቀቅ እንደሚተጉ ተናግሯል። በግሉም ራሱን በማሻሻል ትልቅ ተጫዋች የመሆን ህልሙን ገልጿል። ” ትልቅ ተጫዋች የመሆን አላማ አለኝ። ጠንክሬ በመስራት በውጪ ሀገራት ክለቦች የመጫወት እና ለብሔራዊ ቡድን ከወጣት ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ድረስ መጫወት እፈልጋለው። ትልቅ ተጨዋች ለመሆን ካሰብክ እና አላማ ካለህ አዕምሮህን የፕሮፌሽናል አስተሳሰብ እንዲኖረው ማድረግ አለብህ። በትንሽ አድናቆት እና ሙገሳ አላማህን የምትስት ከሆነ ወደዚህ ህይወት የገባህው ለአላማ ሳይሆን በአጋጣሚ እንጂ ፈልገህ አይደለም ማለት ነው። ስለዚህ አሁን ባለኝ አቋም ተዘናግቼ አልቀመጥም። በዚህ እድሜ ይህን መስራት ከቻልኩ ነገ ከነገህ ወድያ ደግሞ የተሻለ ነገር መስራት እንደምችል ስለማስብ ጠንክሬ ስራዬን በመስራት አላማዬን ለማሳካት እጥራለው ። “
2ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/32852
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
32bf7f749e17c5a796cd6750249ea6d3
45c4e4d56e1e76b62129d9bf91423810
ቅድመ ዳሰሳ | ወልዋሎ ከ ወላይታ ድቻ
በመጀመርያው ሳምንት ሙሉ ሶስት ነጥብ አግኝተው በሊጉ አናት የሚገኙት ክለቦች የሚያገናኘውን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።በመጀመርያው ሳምንት ከሜዳቸው ውጭ ሰበታ ከተማን አሸንፈው የተመለሱት ቢጫ ለባሾቹ በነገው የሜዳቸው ጨዋታ ትልቅ ግምት ይሰጣቸዋል።በአዲስ አበባ ዋንጫ ላይ ጥሩ የውድድር ግዜ ያላሰለፉት ወልዋሎዎች በመጀመርያው ሳምንት ወሳኝ ድል አስመዝግበው በጥሩ የአሸናፊነት መንፈስ ላይ ይገኛሉ። በቅድመ ውድድር ላይ ከተጠቀሟቸው ተጫዋቾች ብዙም ለውጥ ሳያደርጉ የአጨዋወት እና የቅርፅ ለውጥ ብቻ አድርገው የሜዳ ውጭ ጨዋታቸውን ያካሄዱት ወልዋሎዎች የነገው ጨዋታ በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት እንደመሆኑ የማሸነፍ ጫናው የሚኖረው በእነሱ ላይ ነው። በዚህም ከመጀመርያው ሳምንት በተለየ አጨዋወት ማጥቃት ላይ መሠረት አድርገው እንደሚገቡ ይጠበቃል።ቢጫ ለባሾቹ በነገው ጨዋታ ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ጋር ከሌለው ጁንያስ ናንጋጁቦ ውጭ በጉዳት እና በቅጣት የሚያጡት ተጫዋች የለም።በመጀመርያው የሊጉ መርሃ ግብር የቅርብ ተቃናቃኛቸው ሲዳማ ቡናን አሸንፈው ከተጋጣሚያቸው ወልዋሎ በእኩል ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች ምንም እንኳ ጨዋታው ከሜዳቸው ውጭ ቢሆንም ቀላል ግምት አይሰጣቸውም። የጦና ንቦች የቅድመ ውድድር ጊዜያቸው ባሳለፉበት እና በመጠኑ በተላመዱት የመጫወቻ ሜዳ መጫወታቸው ለቡድኑ ጥሩ ዕድል እንደሆነ ቢታሰብም ወሳኝ አጥቂያቸው ባዬ ገዛኸኝ በጉዳት ማጣታቸው ለቡድኑ ጥሩ ዜና አይደለም።አንዳንዴ በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ተመስርተው ሲያስፈልግም በረጃጅም ኳሶች ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ለመጠጋት የሚሞክሩት ወላይታ ድቻዎች በነገው ጨዋታ የመሃል ሜዳ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ለመውሰድ ይቸገራሉ ተብሎ ባይጠበቅም ጠጣሩ የወልዋሎ የመከላከል ክፍል ለማለፍ ግን ይቸገራሉ ተብሎ ይገመታል። በተለይም ቡድኑ ፈጣኑ አጥቂ ባዬ ገዛኸኝ እና በትግራይ ዋንጫ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳየው በረከት ወልዴን በጉዳት ማጣቱ በአጨዋወቱ ላይ ለውጥ ለማድረግ ይገደዳል።የጦና ንቦች በጉዳት ምክንያት የበረከት ወልዴ እና ባዬ ገዛኸኝ አገልግሎት የማያገኙ ሲሆን የተስፋዬ አለባቸው መሰለፍም አጠራጣሪ ነው።የእርስ በርስ ግነኙነት– ቡድኖቹ በሊጉ አራት ጊዜ ተገናኝተው በአስገራሚ ሁኔታ አራቱንም በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።– ስድስት ጎሎች በተቆጠሩበት የሁለቱ ግንኙነት ሁለቱም ቡድኖች ሦስት ሦስት ጎሎችን አስቆጥረዋል።ግምታዊ አሰላለፍወልዋሎ (4-2-3-1)ዓብዱልዓዚዝ ኬይታገናናው ረጋሳ – ፍቃዱ ደነቀ – ዓይናለም ኃይለ – ሳሙኤል ዮሐንስክብሮም ዘርዑ – አቼምፖንግ አሞስሰመረ ሃፍታይ – ካርሎስ ዳምጠው – ምስጋናው ወልደዮሐንስኢታሙና ኬይሙኔወላይታ ድቻ (4-1-4-1)መክብብ ደገፉያሬድ ዳዊት – ደጉ ደበበ – አንተነህ ጉግሳ – እዮብ ዓለማየሁተስፋዬ አለባቸውዘላለም ኢያሱ – ኢድሪስ ሰዒድ – ነጋሽ ታደሰ – ቸርነት ጉግሳዳንኤል ዳዊት
2ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/52431
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1f2e0b86fc0e737fdb5b9007c457bdc7
8d91c4f21dd720951ca100b9044c57e5
ቻይና የኢንተርኔት ነጻነትን በማፈን ዘንድሮም ከአለም አንደኛ ናት
ሁዋዌ በ5ጂ ኢንተርኔት ፍጥነት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥና ስለላን ጨምሮ ሌሎች ነጻነትን የሚጋፉ እርምጃዎችን በመውሰድ የዜጎችን የኢንተርኔት ነጻነት በማፈን ላለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት ከአለም አገራት ቀዳሚነቱን ይዛ የዘለቀችው ቻይና፣ ዘንድሮም በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ተዘግቧል፡፡ፍሪደም ሃውስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም በ56 የአለም አገራት ያካሄደውን ጥናት መሰረት በማድረግ ሰሞኑን ያወጣውን አለማቀፍ የኢንተርኔት ሁኔታ አመላካች ሪፖርት ጠቅሶ ዴይሊ ሜይል እንደዘገበው፣ ቻይና በአመቱ እጅግ የከፋውን የኢንተርኔት ነጻነት አፈና በመፈጸም ቀዳሚነቱን ስትይዝ፣ ኢራንና ሶርያ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ይከተላሉ፡፡በሪፖርቱ የዜጎችን የኢንተርኔት አገልግሎት ነጻነት በማክበር ከአለማችን ቀዳሚዋ አገር ተብላ የተጠቀሰችው አይስላንድ ስትሆን፣ ኢስቶኒያና ካናዳ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡በሌላ ዜና ደግሞ፣ የቻይናው የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ፣ በ5ጂ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘገበበትንና በሰከንድ ከ2.92 ጊጋ ባይት በላይ ፍጥነት ያለውን አዲስ ኔትወርክ በስራ ላይ ማዋሉን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ሁዋዌ ከቱርክ ቴሎኮም ኩባንያ ጋር በመተባበር በኢስታምቡል ይፋ ያደረገው ይህ እጅግ ፈጣን የሞባይል ኔትወርክ፣ በሁዋዌ ሜት ኤክስ ስማርት ፎን አማካይነት ተሞክሮ በፍጥነት አዲስ የአለም ክብረወሰን ማስመዝገቡ ታውቋል፡፡ ኩባንያው ይህንን እጅግ ፈጣን ኔትወርክ በስራ ላይ ለማዋል የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሙን ማስታወቁን የዘገበው ዘ ጋርዲያን፤ ይህ አዲስ እምርታ ኩባንያው ከአሜሪካ መንግስት እየተደረገበት ያለውን ጫና ተቋቁሞ በአለማቀፉ የሞባይል ስልኮች ገበያ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም አመልክቷል፡፡
4ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=24492:%E1%89%BB%E1%8B%AD%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%89%B0%E1%88%AD%E1%8A%94%E1%89%B5-%E1%8A%90%E1%8C%BB%E1%8A%90%E1%89%B5%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%9B%E1%8D%88%E1%8A%95-%E1%8B%98%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%88%AE%E1%88%9D-%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%8A%9B-%E1%8A%93%E1%89%B5&Itemid=212
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
9f0127d47b0d527380a787edc7d55729
d7bbbd82a635b0c8f7f1eeaceeb99b00
የህግ ማስከበር ዘመቻውን የተሳሳተ ትርጓሜ የመስጠት ዝንባሌ እንዳለ ተገለፀ
የአዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ የተሳሳተ ትርጓሜ የመስጠት ዝንባሌ እንዳለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ህግን የማስከበር ዘመቻን አስመልክቶ በሚተላለፉ የተሳሳቱ መልእክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ማብራሪያ ከሰጠባቸው ጉዳዮች ውስጥም “ኢትዮጵያ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እየገባች ነው” የሚለው አንዱ ነው።የህግ ማስከበር ዘመቻው ግልፅ እና የተወሰነ ግብ ያለው ነው ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ፥ ዋናው አላማውም የፅንፈኛው ህወሓት አባላትን ለህግ ማቅረብ ነው፤  ዘመቻውም በቅርቡ ይጠናቀቃል ብሏል።“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ከተሞችን እየደበደበ ነው እና ሰራዊቱ መቀሌን በአየር እየደበደበ ነው የሚለው ሌላኛው የተሳሳተ መሆኑን በመጥቀስ ማብራሪያ የሰጠበት ነው።እንዲሁም “በመቀሌ ከተማ በሚካሄደው ዘመቻ ምህረት የለም” ተብሏል በሚል የሚሉ የተሳሳቱ ትርጓሜ የተሰጠባቸው መረጃዎች መሰራጨታቸውንም አስታውቋል።
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8b%98%e1%88%98%e1%89%bb%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b3%e1%88%b3%e1%89%b0-%e1%89%b5%e1%88%ad%e1%8c%93/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
bcbeb7053ea48465d2e89a4e0dd93ff0
b96c0fdb0395033fd4afbbb55c746e59
ወልዋሎ ከሦስት ተጫዋቾች ጋር ለመለያየት ተስማማ
በጥር ዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ከፍቃዱ ደነቀ፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ምስጋናው ወልደዮሐንስ ጋር ለመለያየት በቃል ደረጃ ተስማምተዋል። በቀጣይ ቀናትም ሒደቱ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።ባለፈው የክረምት ዝውውር መስኮት ቡድኑን ተቀላቅለው ላለፉት ስድስት ወራት ክለቡን ያገለገሉት እነዚህ ሦስት ተጫዋቾች በቀድሞ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቡድን ውስጥ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች እንደነበሩ ይታወሳል።በክረምቱ ከመጀመርያ ፈራሚዎች አንዱ የነበረው ምስጋናው በመጀመርያው ዙር በቀኝ ተከላካይ መስመር ተቀዳሚ ተመራጭ ሆኖ በሁሉም ጨዋታዎች ተሰልፎ ተጫውቷል። ሁለተኛው በስምምነት የተለያየው ተከላካዩ ፍቃዱ ደነቀ በጉዳት ከሜዳ እስከራቀበት ግዜ ድረስ የተከላካይ ክፍሉን በቋሚነት የመራ ሲሆን በተወሰኑ ጨዋታዎችም በአማካይነት ተሰልፎ ቡድኑ ማገልገሉ ይታወሳል። ሶስተኛ ከቡድኑ ጋር በስምምነት የሚለያየው ካርሎስ ዳምጠው ቡድኑ በሊጉ ጅማሬ ላይ ላሳየው ወጥነት ያለው ብቃት ጥሩ አበርክቶ የነበረው ሲሆን በግማሽ ዓመት የቡድኑ ቆይታው ሁለት ጎሎች በማስቆጠር እና ሁለት በማመቻቸት በአራት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል።© ሶከር ኢትዮጵያ
2ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/56946
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
7eda1e6602019899691812e71a17598b
2e4de83a6859c4342ceaa557e5a33f0c
ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞችንና ቅርሶች ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል- ጠ/ሚ ዐቢይ  
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞችንና ቅርሶች ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር ማስመስከሩን ገልፀዋል።የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር አሳይቷል ብለዋል።ጁንታው ካስታጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቀሌ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ አድርጓል፤ ይህም የሠራዊቱን ድልና የጁንታውን ሽንፈት አፋጥኖታል ሲሉም ገልፀዋል።ስግብግቡ ጁንታ በየትኛውም መመዘኛ ለትግራይ ሕዝብ አይመጥነውም፤ የትግራይ ሕዝብ ከእውነት ጋር በመቆምና የጁንታውን እኩይ ዓላማ በመፃረር ከቀበሌ ቀበሌ፣ ከዞን ዞን መቀሌ እስኪገባ ድረስ ተመሳሳይ ድጋፍ ለሠራዊቱ ሰጥቷል።“ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ጁንታው በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን እያወደመ ሄዷል፤ በዚህም የገዛ ወገኑ  ጠላት መሆኑን አሳይቷል ብለዋል።“ጁንታው እኔ ከሞትኩ ብሎ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።“በዚህ ዘመቻችን ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%88%95%e1%8b%9d%e1%89%a5-%e1%8a%a8%e1%88%b5%e1%8c%8d%e1%89%a5%e1%8c%8d%e1%89%a1-%e1%8c%81%e1%8a%95%e1%89%b3-%e1%8c%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%95/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
7954b9dd4aea0c9ef39c5deb692cc041
643fdde2d514254785da049a8cce4ee4
አዴፓ የከሸፈውን መፈንቅለ መንግሥት ያቀነባበሩትና የመሩት "የእናት ጡት ነካሾች" ናቸው አለ
በመግለጫው ላይ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተካሄደውን የከፍተኛ አመራሮች ግድያና መፈንቅለ መንግሥቱን ያቀነባበሩና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትንም አውግዟል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፓርቲ ከታገለባቸው ጉዳዮች መካከል "የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር" መሆኑን አስታውሶ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች ከታሰሩበት ነፃ እንዲወጡ በግምባር ቀደምትነት የታገሉትን አመራሮች "በግፍና በጭካኔ መግደል የእናት ጡት ነካሽነት እና ክህደት" ነው በማለት ድርጊቱን አውግዟል። • "ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት'' • በኢትዮጵያ የኤሊ አደን ለምን አየተበራከተ መጣ? • በፌስታል ተጥላ ለተገኘችው ልጅ የጉዲፈቻ ጥያቄዎች ጎረፉላት አክሎም "በከሸፈው መፈንቅለ-መንግሥት የተፈፀመው ጥቃትና ወንጀል እንዲሁም የአመራሮቻችን የግፍ አገዳደል የአማራን ሕዝብ ያሳፈረና ያዋረደ ሆኖ ሳለ ወንጀሉን ለመሸፋፈን እና ለማሳነስ ሆነ ተብሎ አሉቧልታ በመንዛት ህዝባችንን ለማደናገር እና አቅጣጫ ለማሳት የምትሰሩ አካላት ከዚህ ዕኩይ ድርጊታችሁ ተቆጠቡ" ሲል አሳስቧል። የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ በከሸፈው መፈንቅለ-መንግሥት እጃቸው ያለበትን ግለሰቦችና ቡድኖች በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ሥራው በሁሉም አካላት ርብርብ "በአጠረ ጊዜና በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን" ጠቅሶ "አሁንም ወንጀለኞችን ሙሉ በሙሉ በህግ ቁጥጥር ስር የማዋልና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል" ሲል አስታውቋል። በክልሉ በተደጋጋሚ የታዩ የሰላም መደፍረሶችን በማንሳትም የፀጥታ መዋቅሩን መልሶ ለማጠናከርና በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ "በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ አስፈላጊው ሁሉ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል" ብሏል። ድርጅቱ ውስጣዊ አንድነቱ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንደሚገኝ አስታውሶ የድርጅቱን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የክልሉንና የኢትዮጵያን ሕዝቦች፤ "ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆም የተፈጠረውን ፈተና" በብቃት ለማለፍና አገራችንን ለመታደግ በፅናት እንድትቆሙ" በማለት ጥሪውን አቅርቧል። አክሎም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ አካላት መረጋጋትን፣ ሠላምና አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ላይ በማተኮር በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው አስታውሷል። በመጨረሻም የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በአማራ ክልልና ሕዝብ ላይ ብቻ የተፈፀመ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑን በመግለፅ በዚህ ወቅት ከጎኑ የነበሩትን በአጠቃላይ አመስግኗል።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
11b2c9a4ae24fe495ca1eb3ce6c3d962
7fd45e870d50fd356cdf0e54a44b5675
ደኢህዴን በሁሉም የልማት መስኮች አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገለጸ
ባለፈው ዓመት የተካሔደውን የጥልቅ ተሀድሶ ንቅናቄ ተከትሎ በክልሉ በሁሉም የልማት መስኮች አበረታች ውጤት መመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡ማዕከላዊ ኮሚቴው ሰሞኑን ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማስተላለፉም ተመልክቷል፡፡የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት ባላፈው ዓመት የተካሔደውን የጥልቅ ተሀድሶ ንቅናቄ ተከትሎ በክልሉ በልዩ ልዩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ማዕከላዊ ኮሚቴው ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ የህዝቦችን አንድነት የሚጻረሩ እና ለሰላም እጦት ምክንያት የሚሆኑ አመለካከቶች እና ተግባራትን በዝርዝር ፈትሿል፡፡ በዚህም በአንዳንድ አካባቢዎች ተስተውለው የነበሩ የጠባብ ብሔርተኝነት አመለካከቶች እና ተግባራት እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይህም የጥልቅ ተሀድሶው ውጤት መሆኑን አቶ ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት ረገድ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውንም ማዕከላዊ ኮሚቴው ለይቷል፡፡ ከጥልቅ ተሀድሶው ወዲህ በሙስናና ብልሹ አሰራር ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል የተባሉ 672 አመራሮች እና ባለሙያዎችን መለየት የተቻለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 8ቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ 17ቱ ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ አመራሮች መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡52 ሚሊየን የባከነ የህዝብና የመንግስት ገንዘብም ተመላሽ የተደረገ ሲሆን በገጠር እና በከተማ አለአግባብ ሊባክን የነበሩ በርካታ መሬቶችንም ማስመለስ ተችሏል ብለዋል፡፡በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች በእውቀት እና በምክንያት ላይ ተመስርተው ሀሳቦቻቸውን እና አመለካከቶቻቸውን በጉልህ ማንፀባረቅ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ማሳተፍ መቻሉንም ማዕከላዊ ኮሚቴው በበጎ ጎኑ ገምግሟል፡፡የክልሉን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃርም 6 መቶ ሺ ወጣቶችን በቋሚና በጊዜያዊ የስራ እድል ለማሳተፍ ታቅዶ 520 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከነዚህ መካከል 386 ሺ ወጣቶች በተመረጡ ፓኬጆች በቋሚ የሥራ እድል የተሳተፉ መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡በተለያዩ ተቋማት በሚሰጡ አገልግሎቶች ተሃድሶው ያመጣቸው ለውጦች ቢኖሩም የህዝቡን እርካታ በሚያረጋግጡበት ደረጃ ላይ ባለመሆናቸው ተሃድሶው የበለጠ ግለቱን ጠብቆ መሄድ እንዳለበት አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል፡፡በተያዘውም በጀት ዓመት በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ የክልሉ ህዝቦች በየደረጃው የጀመሯቸውን ትግሎች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማዕከላዊ ኮሚቴው ጥሪ ማቅረቡንም ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ 
5ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/29374/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e2a0a1833ef44918be871051a7ba36c6
fd77c9e3808683d3833bd3218848e35c
“ዝክረ መለስ” የውይይት መድረክ ተካሄደ
– የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ በገንዘብና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የነበራቸው የአመራር ሚና፣ ለብሔራዊ ክልል መንግስታት የነበራቸው ትኩረት እንዲሁም ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሰብዕናቸው ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡“ዝክረ መለስ” በሚል ርዕስ ዛሬ በሸራተን አዲስ በተካሄደው ውይይት ላይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሱፍያን አህመድ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አያሌው ጎበዜ እና የመለስ ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አዜብ መስፍን  የመወያያ ፅሁፎቹን አቅርበዋል፡፡የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በገንዘብና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ የነበራቸውን የአመራር ሚና በተመለከተ በሽግግር ዘመን (1984 – 1987) ፣በተሃድሶ ዘመን (1988 – 1993) እና የፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ትግበራ ዘመን (1994 ወዲህ) በሚል በሶስት ዘመናት የተከፋፈለ የመወያያ ፅሁፍ አቶ ሱፍያን አቅርበዋል፡፡    በሽግግር ዘመን በአገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስርዐት ያልነበረትና ምርትና አግልግሎት ሰጪ ተቋማት እጥረት ይታዩ የነበረበት ወቅት መሆኑን ያስታወሱት አቶ ሱፍያን እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ አቶ መለስ ሳይንሳዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ አዳዲስ ፕሮግራሞችንና የመዋቅር ዝርጋታዎችን ለማምጣት የተንቀሳቀሱበት ጊዜ ነበር ብለዋል፡፡በተሃድሶ ዘመን መለስ በዋናነት ትኩረቱን አገሪቱ አሁን የምትመራባቸውን ዝርዝር ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ያዘጋጁበት ወቅት ነበር ያሉት አቶ ሱፍያን በተጨማሪም በዚህ ወቅት አጋጥመው የነበሩ የኢህአዴግ የውስጥ ችግሮችንና የኤርትራን ወረራ በበሳል አመራር የተወጡበት ጊዜ ነበር ብለዋል፡፡           ከዚህ በኋላ ባሉት ጊዜያት የአቶ መለስ ትኩረት ሶስት የአምስት ዓመት እቅዶች በመንደፍና የፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ትግበራን በቅርበት በመከታተል አገሪቱ ፈጣንና ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የቻለችበት ወቅት ላይ መድረስ ተችሏል በማለት ፁሁፋቸውን አጠቃለዋል፡፡አቶ መለስ ለብሔራዊ ክልል መንግስታት የነበራቸው ትኩረት በተመለከተ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አያሌው ጎበዜ በበኩላቸው የፌዴራል ስርዓት እንዲተገበር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡ በተለይም የክልሎችን አቅም በመገንባትና ፍትሃዊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በሁሉም ክልሎች እንዲዳረስ አቶ መለስ ሰፊ ስራ ሰርተዋል ሲሉ አቶ አያለው ተናግረዋል፡፡የአቶ መለስን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሰብዕና በተመለከተ ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ ባቀረቡት ፅሁፍ መለስ በዓላማ የሚያምን፣ ለስኬቱም በማይሰስት ቸርነት ሙሉ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ሁለንተናዊ እሱነቱን ሰጥቶ ከራስ በላይ ለሆነ አላማ እስከ ህልፈቱ ታምኖ የኖረ ሰው ነው ብለዋል፡፡ወ/ሮ አዜብ አክለውም መለስ የህዝቦችን ሰብአዊና ዜግነታዊ የማይገሰስ ክቡርነት ብሎም ምትክየለሽ ወሳኝነት መቆምያው ያደረገ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተላበሰ መሪ ነበር ሲሉ አጠቃለዋል፡፡ድምፂ ወያነ ትግራይ ሬዲዮ ያዘጋጀው ይህ “ዝክረ መለስ” የተሰኘው የውይይት መድረክ ላይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ እንግዶች የተገኙበት ሲሆን በቀረቡት ፅሁፎች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡
5ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/24717/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
eb19f1f66a68b5f478ab5365d427dd42
b3cad7fd9301c06780d61e8df8e410db
አለም ዓቀፉ የህፃናት አድን ድርጀት ለባህርዳር ከተማ የ42 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አለም ዓቀፍ የህፃናት አድን ድርጅት ለባህርዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚውል 42 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።በተደረገው ድጋፍ ዙሪያ የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የባህርዳር ከተማ ክፍለ ከተሞች ኃላፊዎች በተገኙበት ወይይት ተደርጓል።የምዕራብ አማራ የህጻናት አድን ድርጀት ስራ አስኪያጅ ሙሉቀን እማኙ ድርጀቱ በሀገሪቱ ስድስት ከተሞች ማለትም አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ እና ጅግጀጋ ለተጎጂዎች በምግብ፣ ውሃ እና ጤና ዘርፎች እርዳታ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።በዛሬው ዕለትም በባህርዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለችግር የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ የህበረተሰብ ከፍሎች የ42 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።ከ42 ሚሊየን ብር ድጋፍ ውስጥ 36 ሚሊየን በቀጥታ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጥ እና ቀሪው ለጤና እና ለውሃ አገልግሎት እንደሚውል ነው የተናገሩት።በድጋፋ 5 ሺህ 536 አባወራዎች እና እማወራዎች እንዲሁም 22 ሺህ 144 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው ስራ አስኪያጁ የገለፁት።የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ በበኩላቸው፥ አለም ዓቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በቀጣይም በትክክል መረዳት የሚገባቸውን ሰዎች መመልመቻቸውን የሚያረጋግጥ ግብረ ሀይል ከሰራተኛ ና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ከጤና፣ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ እና ከውሃ ተቋማት መቋቋም አለበት ብለዋል።በናትናኤል ጥጋቡየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%9d-%e1%8b%93%e1%89%80%e1%8d%89-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8d%83%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%8c%80%e1%89%b5-%e1%88%88%e1%89%a3%e1%88%85/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
9605fc7f4dea7087a6be5eb3d7133333
6256645ebd1558725e419af20bc76cf7
በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ 12 የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ከተሞች በየጊዜው የሚገጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት ማስተር ፕላን ተነደፈ፡፡ አዲሱን ማስተር ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡‹‹አዲስ አበባና ዙሪያዋ የኤሌክትሪክ ዲስትሪቢውሽን ማስተር ፕላን ጥናት ፕሮጀክት›› በሚል ስያሜ የተነደፈው ማስተር ፕላን፣ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በማስተር ፕላኑ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ እንደተናገሩት፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2017 ድረስ ተግባራዊ በሚደረገው የአጭር ጊዜ ዕቅድ አሮጌ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ይለወጣሉ፡፡በአጠቃላይ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ቢሊዮን ዶላር በጀት መያዙ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ውስጥ እ.ኤ.አ. እስከ 2017 ለሚተገበረው የአጭር ጊዜ ዕቅድ ማስፈጸሚያ 285 ሚሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ. ከ2018 እስከ 2022 ተግባራዊ ለሚሆነው መካከለኛ ዘመን ዕቅድ ማስፈጸሚያ 37 ሚሊዮን ዶላር፣ ለረዥም ጊዜ ዕቅድ ማስፈጸሚያ (እ.ኤ.አ. ከ2023 እስከ 2034) 745 ሚሊዮን ዶላር መበጀቱ ተገልጿል፡፡በአጠቃላይ በአዲስ አበባና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎትና ዕድገት ለማጣጣም የተያዘውን ዕቅድ ለማስፈጸም፣ 1,067 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ተገምቷል፡፡ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚደረገው በአዲስ አበባ በሚገኙት አሥር ክፍላተ ከተሞችና በኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚገኙት አዲስ ዓለም፣ ኢሉ፣ ወልመራ፣ ሙሎ፣ ሱሉልታ፣ በረህ፣ አሌልቱ፣ ጊምቢቹ፣ አደአ፣ አቃቂ፣ ዓለም ገና፣ ቀርሳና ማሊሞ ወረዳዎች ናቸው፡፡አዲስ አበባና ዙሪያዋ አገሪቱ ከምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 60 በመቶውን እንደሚጠቀሙ ኢንጂነር አዜብ ገልጸው፣ አካባቢዎቹ የሚያጋጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሥርጭት መቆራረጥ ለማስቀረት የፕሮጀክቱ ተግባራዊ መሆን ወሳኝ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ይህንን ማስተር ፕላን ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ያጠናው የእንግሊዝ ኩባንያ የሆነው ፓርሳን ብሪንኤርሆፍ ሊሚትድ ነው፡፡ የኩባንያው ተወካይ ናንካ ብሩስ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፣ አዲስ አበባ በፍጥነት እያደገች በመሆኑ እያጋጠማት ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ወጥታ፣ ለዕድገቷ የሚያስፈልጋትን ኃይል ለማግኘት ማስተር ፕላኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲሆን፣ በከተማው የሚገኙ አሮጌ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያዎች በአዲስ ይተካሉ፡፡ መሻሻል ያለባቸውም እንዲሻሻሉ ይደረጋል በማለት ኢንጂነር አዜብ ተናግረዋል፡፡በቀጣይነት ይህ ፕሮጀክት በሐዋሳ፣ በመቐለ፣ በባህር ዳርና በሌሎች ትልልቅ የክልል ከተሞች ተግባራዊ እንደሚሆን ኢንጂነር አዜብ አስረድተዋል፡፡በአዲስ አበባና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ምክንያት ነው ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ ለኃይል መቆራረጡ የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡
3ቢዝነስ
https://www.ethiopianreporter.com/article/7635
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
07d7420f8082204cbd7cc08e9f0ae06e
ea706fc728a8d5ede01d08d68898d155
ሄርበርት ሁቨር ምን ያህል አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞች ከአውሮፓ ወደ አገራቸው መልሰዋል?
ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስና ጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ። መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው።
null
null
https://huggingface.co/datasets/israel/AmharicQA
ef2e15a52b923d94ee0bd883df396196
6c1067716ca66e9f00b6687e6b6d8061
ባዶ ሆድና ትምህርት
«ምግብ ሳይመገቡ መማር ይከብዳል፤ መምህሩ  የሚለውን  በደንብ አንከታተለውም» ይላል   የአስራ ሁለት መቱ ታዳጊ ዮሐንስ ሙለታ።  ታዳጊው  በኮከበ ጽባህ አጸደ ህጻናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  የስድስተኛ ክፍል  ተማሪ ነው። የቤተሰቦቹ የኑሮ ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት ቁርስና ምሳውን ይመገብ የነበረው በትምህርት ቤቱ ነበር። ዘንድሮ ግን እሱ ምክንያቱን ባያውቀውም በጣም ለባሰባቸው የደሃ ልጆች ብቻ የምግብ አገልግሎት ስለሚሰጥ እሱ ከሳምንቱ አብዛኛውን ቀን በባዶ ሆዱ ለማሳለፍ መገደዱን ይናገራል። እሱ ባይናገርም ነጭ ሆነው የደረቁት ከንፈሮቹ የሆዱን ባዶነት ያሳብቁበታል።በተመሳሳይ በወጣቶች ገነት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው የአስራ ሁለት ዓመቷ አበባ «ምሳ ይዤ አልመጣም፤ ብዙ ጊዜ የምበላው  ከጓደኞቼ ጋር ነው፤ አንዳንድ ጓደኞቻችን ብዙ ቀን ጾማቸውን ይውላሉ፤ የሚያፍሩት ደግሞ ባዶ ምሳ እቃ ይዘው መጥተው ይመለሳሉ።» የምትለው ተማሪ ሀና ትምህርት ሲጀመር ምገባው  በጥቅምት ይጀመራል ቢባልም እስካሁን  ግን ምንም  ነገር የለም።  መምህራኖቻችንን ስንጠይቃቸው በቅርቡ ይጀመራል ይሉናል ትላላች።የትምህርት ቤቱ  የአደረጃጀት ምክትል ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ዘነበ ወርቁ  ከዚህ ቀደም በእናት ወግ በጎ አድራጎት 107 እንዲሁም  በፍቅር ወንድማማቾች የጤና ስፖርት ማህበር 18  ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንደነበሩ በማስታወስ ዘንድሮ  ፍቅር ወንድማማቾች የስፖርት ማህበር ብቻ 3 ሺ ብር በመመደብ 25 ተማሪዎችን  እየመገበ መሆኑን ይናገራሉ። በትምህርት ቤቱ አብዛኛው ተማሪ  ከደሀ ቤተሰብ የመጡ፣ ዘመድ ጋር ተጠግተው የሚኖሩና በትርፍ ሰዓታቸው ሥራ እየሠሩ ራሳቸውን የሚደጉሙ ናቸው። ከልዩ ፍላጎትና ከአጸደ ህጻናት ውጪ ካሉት 1ሺ200 ተማሪዎች አራት መቶ የሚደርሱት የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እንደሆኑ ይናገራሉ።  አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተለይተው እንዲቀርቡለት በጠየቀው መሰረት ከፍተኛ ችግር ያለባቸው 270 ተለይተው የተላኩ ቢሆንም እስካሁን በቅርቡ ይጀመራል ከሚል ምላሽ ውጪ ጠብ ያለ ነገር እንደሌለ ይናገራሉ።የወጣቶች ገነት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር  የሆኑት አቶ ታገል መንግስቱ በበኩላቸው የምገባ ፕሮግራሙ መጀመሪያ ቀን እነሱንም እንደናፈቃቸው ይገልጻሉ። ባለፈው ዓመት  የእናት ወግ በጎ አድራጎት 85 ተማሪዎችን ይዞልን ነበር ዘንድሮ ከመቶ በላይ ምገባ የሚያስፈልጋቸውን ለይተናል።   አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮን ባለፈው ሳምንት ጠይቀን  ይጀመራል ብንባልም የመጣ ነገር የለም። በመሆኑም ብዙ ተማሪዎች በችግር ውስጥ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በጣም የባሰባቸውን እስካሁንም ሲደግፍልን የነበረው ሙላት የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ27 ተማሪዎች የምሳና ቅዳሜ ደግሞ የጥናትና የምሳ ድጋፍ እያደረግልን ይገኛል።ብዙ ቤተሰብ  እንደ አምናው የምገባ ፕሮግራሙ ይኖራል ብሎ ስላልተዘጋጀ ቅሬታ ፈጥሮበታል ይላሉ።«ምገባው በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ይጀመራል» የሚሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህጻናት ጤናና ምገባ ቢሮ አስተባባሪ የሆኑት ወይዘሪት ሜቲ ታምራት ናቸው። ወይዘሪት ሜቲ እንደተናገሩት  ፕሮግራሙ እስካሁን ሲካሄድ የነበረው በተለያዩ አካላት  ድጋፍ ነበር።  በዋናነትም የእናት ወግ በጎ አድራጎት  ማህበር እስከ ባለፈው ዓመት 22 ሺ ተማሪዎችን  በአስሩም ክፍለ ከተማ በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲመግብ ነበር። ሌሎች የተለያዩ ተቋማት፣ መምህራን፣ ማህበረሰቡና ባለሀብቶች ደግሞ ወጥነት ባይኖረውም አስር ሺ  ለሚደርሱ ተማሪዎች አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።  የእናት ወግ የበጀት እጥረት ስለገጠመው በዚህ ዓመት እየመገበ ያለው ዘጠኝ ሺ ብቻ ሲሆን፣ እነዚህም በተለይ ችግሩ በሰፋባቸው አራዳ፣ ቂርቆስና ጉለሌ እንዲሆም በሌሎቹ ክፍለ ከተሞች በተወሰኑ ትምህርች ቤቶች ብቻ ነው።ፕሮግራሙ ውጤታማና አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ከተማ አስተዳደሩ ለመደገፍና ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተደራሽ ለማድረግ መስራት ጀምሯል። በዚህም በ2011 ከተማ መስተዳድሩ በፈቀደው በጀት ፕሮግራሙ 51 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎችን የቁርስና ምሳ ተጠቃሚ ለማድረግ ወስኗል። ለዚህም የመጀመሪያ ዙር  66ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የተፈቀደ ቢሆንም ፋይናንስና ኢኮኖሚ ብሩን ለክፍለ ከተሞች የለቀቀው  ታህሳስ  አምስት ዘግይቶ ነው።ሆኖም በአሁኑ ወቅት ወደ የትምህርት ቤቱ አካውንት እንዲገባ ተደርጓል።    በሴቶችና ህጻናት ጉዳይ በኩልም ምግብ የሚያዘጋጁት እናቶች እንዲደራጁ ተደርገው ወደ ስራ እየገቡ ነው። አንዳንድ ትምህርት ቤቶች  በፍጥነት ጀምረዋል በቅርብ ጊዜ  ደግሞ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚጀምሩ ይሆናል ።ፕሮግራሙ የሚካሄደው ተማሪዎችን ለመርዳት ሳይሆን ህጻናቱ በቂ ምግብ የማግኘት መብት ስላላቸው ነው የሚሉት ወይዘሪት ሜቲ ከዚህ ቀደም  ትምህርት የሚያቋርጡ ክፍል ውስጥ የሚወድቁ እንደነበሩ በማስታወስ  ልጆቹ ተምረው ቢጨርሱም ውጤታማ፣ ጤናማ ብቁ ዜጋም እንደማይሆኑ ይናገራሉ።   በመንግስት የሚደረገው ድጋፍ የማይቆራረጥ በመሆኑ ጥቅሙ ከፍተኛ  ነው የሚሉት ወይዘሪት ሜቲ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ዘንድሮ በከተማዋ ሰባ ሺ የሚደርሱ ተማሪዎች ድጋፉ እንደሚያስፈልጋቸው ተረጋግጧል ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 20/2011በራስወርቅ ሙሉጌታ
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=2170
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
fc8338220645c8156a8ffcd7db92bf9a
66eee7c3a354b9a7a46f761213d1ad84
የሶስትዮሽ ስብሰባው ነገ ይካሄዳል ተብሎ ነበር
ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በአሜሪካ ሊካሂድ የታሰበው ስብሰባ ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች ፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል በአሜሪካ የትሬዠሪ ቢሮ ሴክሬተሪ እና የዓለም ባንክ ፕሪዝዳንት በታዛቢነት የተገኙበት የሶስትዮሽ ድርድር በአሜሪካ ሲካሂድ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አሁንም በአሜሪካ የትሬዠሪ ቢሮ ሴክሬተሪ የተጠራው እና በዋሺንግተን ዲሲ የካቲት 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም ሊካሂድ በታሰበው የሶስትዮሽ የድርድር መድረክ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባላማጠናቀቁ፣ ኢትዮጵያ አልሳተፍም ብላለች፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ በአሜሪካ በመገኘት ውይይቱን ማድረግ እንዳልተቻለ ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ የትሬዠሪ ቢሮ የኢትዮጵያ መንግስት ማስታወቁን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የግብጹ አህራም ኦንላይን እንደዘገበው የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ በስብሰባው ለመታደም ወደ አሜሪካ አቅንተዋል፡፡ በአሁኑ ስብሰባ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቅ እንደነበረም ነው አህራም በዘገባው የጠቆመው፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ትናንት የካቲት 17 ማምሻውን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ጣሊያን ማምራታቸው ይታወቃል፡፡ በነገው እለት በዋሺንግተን ዲ.ሲ. ይካሄዳል በተባለው የሶስትዮሽ ስብሰባ ላይ አቶ ገዱን ጨምሮ የሶስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቅ ነበር፡፡
5ፖለቲካ
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-will-not-participate-on-washington-s-meeting-over-the-gerd
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
c3d3265681d42aa7dd68661d5cfac2e0
32729c489b66f00b9e69535adbc688ae
የጃክ ማ ፋውንዴሽን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ለሶስተኛ ጊዜ ግብዓት መላኩ ተገለጸ
አዲስ አበባ፡- ለሶስተኛ ጊዜ ከጃክ ማ ፋውንዴሽን ለአፍሪካ አገራት የተላከው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብአት ኢትዮጵያ ገብቷል፡፡ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ወደ 61 ሺህ ቶን የሚጠጋ ይህ ቁሳቁስ ለ54 የአፍሪካ ሀገራት የሚከፋፈል እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በውስጡም 199 ሺህ 300 ከንክኪ መከላከያ ልብሶች፣ 300 የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች፣ 708 የሙቀት መለኪያዎች፣ 28 ሺህ 500 የሕክምና ጓንቶች እና 3 ሺህ 800 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች ይገኙበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው፤ የጃክ ማ ፋውንዴሽን ከአፍሪካ ጎን በአጋርነት በመቆሙ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ጃክ ማ በመጀመሪያው ዙር ለእያንዳንዱ የአፍሪካ አገር ቫይረሱን ለመለየት የሚረዱ 20 ሺህ መመርመሪያዎች፣ 100 ሺህ የፊት ጭምብል፣ የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው አንድ ሺህ መከላከያ ልብሶች በሁለተኛው ዙር ደግሞ 500 የመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር)፣ 200 ሺህ የፊት መሸፈኛዎችና የህክምና ሙሉ ልብሶች፣ አንድ ሚሊዮን ናሙና መውሰጃ ፣ ሁለት ሺህ የሰውነት ሙቀት መለኪያ እና 500 ሺህ ጓንቶች ለአፍሪካ አገራት ልከው መከፋፈላቸው ይታወሳል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20/2012በጋዜጣው ሪፖርተ
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=31250
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e5f7a855126e7da0f97f4b902ab2a72e
9b412ec74dcdd37ad659ccebc4887e4e
'አስጸያፊ' ከመባል ኦስካር ወደማሸነፍ
የንጽህና መጠበቂያው ሞዴስ ሲሠራ ትላንት ባልተለመደ ሁኔታ ያለ አስተዋዋቂ የተካሄደው የኦስካር የሽልማት ሥነ ሥርዐት በርካታ ጥቁር ፊልም ሠሪዎች ጎልተው የወጡበት ነበር። 'ብላክ ፓንተር' በምርጥ ኦሪጅናል ስኮር፣ በፕሮዳክሽን ዲዛይንና በኮስቲውም ዲዛይን ሦስት ሽልማቶች አግኝቷል። በተጨማሪም ዛንዚባር የተወለደው የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቀኛ ህይወትና ሥራ የሚዳስሰው ፊልም እንዲሁም፣ ለበርካታ ዓመታት ሽልማት ሳይገኝ የቆየው ስፓይክ ሊ ተሸልሟል። ሌላው ተሸላሚ የጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ላይ የሚያተኩረው ዘጋቢ ፊልም ነው። በሥራው ከተሳተፉት አንዷ ደግሞ ስኔህ ትባላለች። ስኔህ የወር አበባ ያየችው በ15 አመቷ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባዋ ሲመጣ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አላወቀችም ነበር። "በጣም ደንግጬ ነበር። ከባድ በሽታ የያዘኝ መስሎኝ ማልቀስ ጀመርኩ" በማለት ትናገራለች። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" • በፍቅረኞች ቀን የፍቅር ስጦታ ለሴት ተማሪዎች "ለእናቴ ለመናገር ስለፈራሁ ለአክስቴ ነበር የነገርኳት። አክስቴ 'አሁን አድገሻል ማለት ነው። አታልቅሺ፤ ተፈጥሯዊ ነው።' በማለት አስረዳቺኝ። ለእናቴ የነገረቻት እሷ ናት" ስኔህ አሁን 22 አመቷ ነው። በመንደሯ በሚገኝ የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በሚያመርት አነስተኛ ድርጅት ውስጥ ትሠራች። ስለ ወር አበባ ለህብረተሰቡ ታስተምራለች። ስኔህ ስለ ወር አበባ የተዛባ አመለካከት እንዳለ ትናገራለች 'ኢንድ ኦፍ ሴንቴንስ' (የአረፍተ ነገር መጨረሻ) የተባለው ዘጋቢ ፊልም ኦስካር ሲያሸንፍ፤ ስኔህ የኦስካር ዝግጅትን ለመታደም ወደ ሎስ አንጀለስ አቅንታለች። ዘጋቢ ፊልሙ የተሠራው በሰሜን ሆሊውድ አንድ የተማሪዎች ቡድን ባሰባሰበው ገንዘብ ንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) የሚሰራ ማሽን እና ኢራናዊ አሜሪካዊ ፊልም ሠሪ ራይካ ዜህታብቺን ወደ ስኔህ መንደር በመላክ ነው። ፊልሙ የተቀረፀው በካቲክሄታ መንደር ባሉ የእርሻ ቦታዎች፣ ሜዳዎች እና የትምህርት ክፍሎች ነው። እንደ ሌሎቹ የሕንድ አካባቢዎች ሁሉ በካቲክሄራ መንደርም የወር አበባ የመነጋገሪያ ርዕስ አይደለም። • ሴቶች የተቆጣጠሩት የስፔን ካቢኔ • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች ሴቶች በወር አበባ ወቅት እንደቆሸሹ ስለሚታሰብ ከሀይማኖት ቦታዎች እና ሌሎች ማኅበራው ክንውኖችም ይታገዳሉ። ስለ ወር አበባ ብዙ የተዛቡ አመለካከቶች ስላሉም ሰኔህ የወር አበባ ከማየቷ በፊት ስለ ወር አበባ ምንነት አለማወቋ አይገርምም። "የወር አበባ የመነጋገሪያ ነጥብ አልነበረም፤ በሴቶች መካከልም መወያያ ርዕስ አልነበረም" ትላለች። እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 'አክሽን ኢንዲ' ውስጥ የሚሠራ ሱማን የተባለ ጎረቤቷ ንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) የሚሠራ አነስተኛ ድርጅት ውስጥ ለመሥራት ፈቃደኛ እንደሆነች ጠየቃት። የኮሌጅ ተመራቂ የሆነችው እና አንድ ቀን ለደልሂ ፖሊስ መሥራትን የምታልመው ሰኔህ ጥያቄውን በደስታ ተቀበለች። በመንደሩም "ሌላ ምንም አይነት የሥራ እድል" አልነበረም። 'ፍላይ' የተባለው ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ "እናቴን ፍቃድ ስጠይቃት 'አባትሽን ጠይቂ አለችኝ'። በቤታችን ሁሉም ከባድ ውሳኔዎች በወንዶች ነው የሚወሰኑት" ስኔህ ለአባቷ ስለ ሥራው ለመናገር በጣም አፍራ ስለነበረ የህፃናት መፀዳጃ እንደምትሰራ ነበር የነገረችው። "ሥራውን ከጀመርኩ ሁለት ወር በኋላ ነው እናቴ ለአባቴ የሴቶች መፀዳጃ (ሞዴስ) እንደምሠራ የነገረችው" ትላለች ሰኔህ። እድለኛ ሆና አባቷ " ችግር የለውም፤ ሥራ ሥራ ነው" አለ። • ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ • መጠጥ የ130 ሰው ህይወት ቀጠፈ ዛሬ አነስተኛ ድርጅታቸው ከ18 እስከ 31 ዓመት የሆኑ ሰባት ሴት ሠራተኞች...
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
faa284db65971f6ae60229a731d7e75d
12971878e68d0213c0485c7b729803c2
የጀርመን ሮማን ካቶሊክ ቤተክርስትያን ቀሳውስት ከፈረንጆቹ 1946-2014 ባለው ጊዜ 3600 ገደማ ሕፃናት ላይ ፈፅመውታል የተባለው ጭቆና ይፋ ሆኗል።
የጀርመን ቄሶች ሕፃናት ላይ የፈፀሙት በደል ይፋ ሆነ\nጥናቱን ያካሄደው የጀርመን ሮማን ካቶሊክ ቤተክርስትያን ኦፊሴላዊ ውጤቱን መስከረም 25 ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ዘገባው እንደሚጠቁመው 1670 ገደማ የቤተክርስቲያኒቱ ሰዎች 3677 ሕፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት አድርሰዋል። • የ80 ሚሊየን ዶላር የሙስና ቅሌት ተጋለጠ የቤተክርስትያኒቱ ቃል አቀባይ የሆኑ ግለሰብ በውጤት 'እጅግ ማፈራቸውን እና ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን' ተናግረዋል። ጥናቱ 'ግፍ ፈፃሚ ቀሳውስት አሏት' እየተባለች ለምትታማው የሮማን ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሌላ መዘዝ ይዞ ብቅ ብሏል። ከጥቃት አድራሽ ቀሳውስት መካከል 38 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ቅጣት የተጣለባቸው የሚል ዘገባም ብቅ ብሏል፤ ከስድስት አንድ ብቻ ናቸው ለፍርድ የሚቀርቡት። ጥቃት ከደረሰባቸው ሕፃናት መካከል በርካቶቹ ወንዶች እንደሆኑ ሲነገር ዕድሜያቸው ደግሞ ከ13 ዓመት በታች ነው ተብሏል። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ጥናቱን ያካሄዱት ሦስት የጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ 38 ሺህ ያህል መዝገቦች አገላብጠዋል፤ በርካታ መዝገቦች እንደተደመሰሰ ቢጠረጠርም። የቤተክርስቲያኒቱ ቃል አቀባይ የሆኑት ቢሾፕ ስቴፋን አከርማን «የጥናቱ ዓላማ በቤትክርስትያናችን እየተፈፀመ ያለውን ግፍ ማስቆም ነው» ብለዋል። የሮማን ካቶሊክ ቤ/ክ ዋና መቀመጫ የሆነችው ቫቲካን ስለጉዳዩ እስካሁን ምንም ባትልም ሊቃ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ግን ስለጉዳዩ ለመምከር ለወርሃ የካቲት ቀጠሮ መያዛቸው እየተነገረ ነው። • በሄይቲ የኦክስፋም ቅሌት፡ ተጠርጣሪዎች የአይን እማኞችን አስፈራርተዋቸዋል
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
f87dbaa84e56327601a5cb04071df48c
ed2a6583cd32aef33563b2a748f5adce
የአሜሪካ ዶላር ቅቡልነት ማክተሚያ እየተቃረበ መሆኑን ብሎምበርግ ዘገበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2012 ዓ.ም (አብመድ) ለ60 ዓመታት የአብዛኞቹ ሀገራት የመጠባበቂያ የባንክ ክምችት መለኪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካ ዶላር ቅቡልነት እያከተመ እንደሆነ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ የአሜሪካውያን የኑሮ ሁኔታ ለዓለም ሚዛን ሆኖ መቆየቱ የዶላርን ቅቡልነት ማስቀጠሉን ያመለከተው ዘገባው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተደቆሰው የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት የኑሮ ሚዛንነቷን ማሳጣቱን ገልጧል፡፡ከአሜሪካ ምጣኔ ሀብት መዳከም በተጨማሪ ሀገሪቱ እንደ ልዩ አድራጊ ፈጣሪ የመቆጠሯ ጉዳይም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ብሉምበርግ አመላክቷል፡፡ የሀገራት ውስጣዊ የምጣኔ ሀብት መሠረትና በውጭ ሀገራት የአሜሪካ የጥንካሬና ድክመት ሁኔታ ምዘና የዶላርን ቅቡልነት ማብቂያ የሚያመለክቱ እንከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተፅዕኖ አስቀድሞም የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት ማሽቆልቆል እንደጀመረ ያስታወሰው ዘገባው በዚህ የአውሮፓውያን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሀገራዊ የቁጠባ መጠን 1 ነጥብ 4 ከመቶ እንደነበርና ይህም በሀገሪቱ ታሪክ 5ኛው ዝቅተኛ የቁጠባ መጠን የተመዘገበበት እንደሆነ አብራርቷል፡፡የሀገራት ባንኮች በዶላር መጠባበቂያ ገንዘባቸውን ስለሚያስቀምጡ ግን ሳያውቁት አሜሪካን ይደጉማሉ፤ በዚህም በቂ ቁጠባ ከውጭ ታገኛለች፡፡ የውጭ ኢንቨስትመንት ስበቷ ግን ከ1982 (እ.አ.አ) ጀምሮ እየቀነሰ እንደሆነ ነው የተመላከተው፡፡የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና የቁጠባ መውረድ ከኮሮናቫይረስ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ጋር ተዳምረው የአሜሪካን ዶላር የበላይነት እንደቀነሱት ታውቋል፡፡ የዚህ ዓመት የበጀት ጉድለት እስከ 19 ነጥብ 9 በመቶ እንደሚሆንም ተገምቷል፤ በእርግጥ በቀጣዩ የአውሮፓውያን በጀት ዓመት ወደ 9 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚወርድ ተስፋ ተደርጓል፡፡በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሚሊዮኖች ሥራ ማጣታቸው ደግሞ የበለጠ የበጀት ጉድለት መንስኤ እንደሚሆን ተመላክቷል፤ የሥራ ማጣቱ የቁጠባ መጠንን በእጅጉ ይቀንሰዋልና፡፡ የቁጠባ መጠን በሂደት ከዜሮ በታች 10 ሊደርስ እንደሚችልም ተሰግቷል፡፡ ይህ ደግሞ በአሜሪካ የምጣኔ ሀብት ታሪክ ታይቶ የማያውቅ አደጋ ያስከትላል፡፡በዚህም ቀውስ ውስጥ ሆኖ የአሜሪካ ዶላር በጥር ከነበረበት የመግዛት አቅም ሚያዝያ ላይ ሰባት ከመቶ ጨምሮ መገኘቱን ያመለከተው መረጃው ዕድገቱ ግን በሌሎች ሀገራት ፍላጎት የተነሳ እንጂ በአሜሪካና በንግድ ሸሪኮቿ ምጣኔ ሀብት መጎልበት የመጣ አለመሆኑን አመላክቷል፡፡በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት ዓለማቀፋዊ ተጽእኖ ፈጣሪነት እንደሚያከትምም እየተገለጸ ነው፡፡ አሜሪካ ተጽእኖ የምትፈጥርባቸው ዓለማቀፍ ተቋማትንና ስምምነቶችን አለማክበርና ራስን ማግለል እንደሚያዳክማትም ነው የተገለጸው፡፡ ከ “ፓሪስ” የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማፈንገጥ፣ ከፓስፊክ ተሻጋሪ አጋርነት (ትራንስ-ፓስፊክ ፓርትነርሺፕ)፣ ከዓለም ጤና ድርጅትና ከነባሩ የአትላንቲክ ጥምረት ራሷን ማግለሏ በአብነት ተጠቅሰዋል፡፡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በአግባቡ መቆጣጠር አለመቻልና በቅርቡ የተከሰተው ማኅበራዊ ቀውስ ከ1960ዎቹ (እ.አ.አ) ወዲህ ሀገሪቱ ዓይታ የማታውቃቸው ችግሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ቀውሶች ደግሞ ከዓለማቀፋዊ መሪነቷ ለመውረዱ ማሳያ ሆነዋል፡፡ምንም እንኳ ምጣኔ ሀብቷ ከመጪው ጥር አካባቢ ጀምሮ ሊያንሰራራ እንደሚችል ቢጠበቅም የቁጠባ አቅሟ በቀላሉ ይጠገናል ተብሎ አልተገመተም፡፡ የዶላር የመግዛት አቅም ከውጭ ንግድ አንጻር በመጪው ሐምሌ እስከ 35 በመቶ እንደሚወርድ መገመቱ ደግሞ ግሽበቱን ለመመከት ፈተና እንደሚሆንባት አስግቷል፡፡የአሜሪካ ዶላር የመግዛት አቅም እንደተተነበየው ከወረደ ደግሞ ሦስት አንኳር ጉዳዮችን ያስከትላል፤ ግሽበት፣ ለተወሰነ ጊዜ በግሽበት ውስጥ መቆየት እና ከቀውሱ ለማገገም ጊዜ መውሰድ፡፡ የእነዚህ ሁሉ ድምር ደግሞ የፋይናንስ ገበያውን በአዙሪት ውስጥ ሊያቆየው ይችላል፡፡ ይህም የአሜሪካን የንግድ ጉድለት ያሰፋዋል፡፡ የንግድ ድጎማ ሥርዓቷ፣ በተለይም ከቻይና ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ባላቸው 102 ሀገራት ላይ የምትከተለው አሠራር መልሶ ራሷን እንዳያዳክማትም ተሰግቷል፡፡የዋሽንግተን ጊዜንና ሁኔታን ያላጤነ ከቻይና የሚጋፈፍ የፋይናንስ ጉድለት አሞላልም መጨረሻው የማገገሚያ ጊዜዋን ሊያራዝመው እንደሚችል ዘገባው ያስረዳል፡፡ብሉምበርግ ዘገባውን ሲቋጭም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝንና የዘረኝነት ቀውሱ የዓለም ምጣኔ ሀብት አድራጊ ፈጣሪውን የአሜሪካ ዶላር መሪነት ያሳጣዋል፤ የአሜሪካንም ምጣኔ ሀብት የከፋ ቀውስ ውስጥ ያስገባዋል ብሏል፡፡ዘገባው የአሜሪካ ዶላር ጥገኛ በሆኑ ሌሎች ሀገራት ላይ ምን ሊከሰት እንደሚችልና ቀጣዩ የአሜሪካ ዶላርን የሚተካ መገበያያ ምን እንደሆነ አላመለከተም፡፡
4ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.amharaweb.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8b%b6%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%89%85%e1%89%a1%e1%88%8d%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%88%9b%e1%8a%ad%e1%89%b0%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%89%b0/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
6ef6aa0ca3e1ce3f3007d42657c5ace9
25a7c27f8b01f1e3f55ba0d590e970e3
በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ያገኙት ነጂብ ማኅፉዝ የምን ሀገር ዜጋ ናቸው?
አብዱልራዛቅ እ.ኤ.አ. በ1994 ላይ ያሳተሙት ‹ፓራዳይዝ› የተሰኘው ልብ ወለድ ታንዛኒያ ውስጥ በ20ኛው ምዕት ዓመት የልጅ አስተዳደግ ምን እንደሚመስል ፍንትው አድርገው ያሳዩበት ነው። በዚህ ልብ ወለድም ዓለም አቀፉን የ‹ቡከር› ሽልማት ለማግኘት መቻላቸውን ቢቢሲ ዘግቦታል፡፡ እንደ የኖቤል ኮሚቴ የሥነ ጽሑፍ ክፍል አገላለጽም፣ ‹‹[የእሳቸው] ገጸ ባህርያት ሁሌም ቢሆን በባህልና አኅጉራት መካከል የሚሽከረከሩ፣ በአሁን ሕይወትና በመጪው ሕይወት መካከል የሚመላለሱ ናቸው። በቀላሉ ሊያልፉት የማይችሉት ከባድ እውነታ ውስጥ ናቸው፡፡›› እ.ኤ.አ. በ1948 በዛንዚባር የተወለዱት አብዱልራዛቅ፣ እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ መገባደጃ አገረ እንግሊዝ የገቡት ስደተኛ ሆነው ነው። በቅርቡ ጡረታ እስከወጡበት ዕለት ድረስ በካንተርበሪው የኬንት ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛና የድኅረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፎች ፕሮፌሰር ነበሩ። ሽልማቱ፣ ደራሲው ያለፉበትን የስደተኞች ቀውስንና ቅኝ አገዛዝን በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲደረግባቸው ያስችላል ብለዋል፡፡ ‹‹እነዚህ በየዕለቱ ከእኛ ዘንድ ያሉ ነገሮች ናቸው። ሰዎች እየሞቱ ነው፣ ሰዎች በዓለም ዙርያ አሁንም እየተጎዱ ነው፡፡ በእነዚህን ጉዳዮች ላይ በፍፁም ቀናነትና አስተውሎት መንገድ መነጋገር መላ መምታት አለብን፤›› ብለዋል የኖቤል ተሸላሚው አብዱልራዛቅ። ዓምና በሥነ ጽሑፍ ያሸነፉት አሜሪካዊው ገጣሚ ሊዊስ ግሉክ መሆናቸው ይታወሳል። የስዊድኑ አካዴሚ በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ከሸለማቸው ታላላቅ ደራስያን መካከል ከአፍሪካ አኅጉር ስድስት ደራስያን ይገኙበታል፡፡ እነርሱም ዎሌ ሾንካ (ናይጀሪያ)፣ ነጂብ ማኅፉዝ (ግብፅ)፣ ናዲን ጎርዲመር (ደቡብ አፍሪካ)፣ ጄ.ኤም ኮትዚ (ደቡብ አፍሪካ)፣ እና ዶሪስ ሌሲንግ (ዚምባቡዌ -እንግሊዝ) ይገኙበታል፡፡
null
null
https://huggingface.co/datasets/israel/AmharicQA
7b8d6ea4eeeb51c6616c2860df2417d2
c4be84dbb4897b2b4d19f91885494e20
7 ኤርትራዊያን ተጫዋቾች ካምፓላ አየር ማረፊያ ላይ ተሰወሩ
በዘንድሮ የሴካፋ ውድድር ላይ በኡጋንዳ የተሳተፈው የኤርትራ ብሔራዊ ቡደን አባላት የሴካፋ ቃል አቀባይ ሮጀርስ ሙሊንደዋ ተጫዋቾቹ የጠፉት ውድድራቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም "ከዚህ ቀደም የሚጠፉት ከሆቴላቸው ነበር። አሁን ግን አየር ማረፊያ ደርሰው 'ቼክኢን'እንደማድረግ፤ መኪና ተከራይተው ከሚጠብቋቸው ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ተሰውረዋል" ብለዋል። ኤርትራውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ለውድድር ከሃገራቸው ከወጡ በኋላ የመጥፋታቸው ዜና ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይም ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከሃገራቸው የወጡ አራት ኤርትራውያን ካረፉበት ሆቴል መጥፋታቸው ይታወሳል። የሴካፋው ቃል አቀባይ ሮጀርስ ሙሊንድዋ ጥቅምት ወር ላይ አራቱ ኤርትራውያን እግር ኳሰኞች የጠፉበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ፤ "በካምፓላ በርካታ ኤርትራውያን አሉ። ኤርትራውያኑ ካሸነፉበት ውድድር በኋላ ሆቴል ድረስ አብሮ በመሄድ ብዙዎች ድጋፋቸውን ሲሰጡ ነበር። ከዛ ተጫዋቾቹ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ተቀላቅለው ነው ከሆቴል የወጡት። እኛ የትኛው ተጫዋች የትኛው ደጋፊ መሆኑን መለየት አልቻልንም ነበር" ይላሉ። የተጫዋቾቹን መጥፋት ሴካፋ ለኡጋንዳ መንግሥት፣ ለኡጋንዳ ስፖርት ፌዴሬሽን እና በኡጋንዳ ለኤርትራ ኤምባሲ ማሳወቁን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። 7ቱ ተጫዋቾች ከሆቴል ሳይሆን አየር ማረፊያ ደርሰው ለምን እንደተሰወሩ ሲያስረዱ፤ "ከየሃገራቱ ጋብዘን የሴካፋ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ያደረግናቸው ሰዎች።" አሉ የሚሉት ቃል አቀባዩ፤ በስም የሚጠቅሷቸው እና ከኤርትራ የመጡት ልዑክ የእግር ኳስ ባለሙያ ሳይሆኑ "የኤርትራ ከፍተኛ ፖሊስ አባል መሆናቸውን ተረዳን" ይላሉ። እኚህ በስም የተጠቀሱት ግለሰብ ተጫዋቾቹ በሚያርፉበት ሆቴል አብረዋቸው ስለነበሩ ተጫዋቾቹ ከሆቴል መሰወር አለመቻላቸውን ተናግረዋል። "ውድድሩ እስኪያበቃ ድረስ ከሆቴሉ መውጣት ያልቻሉት ሲከታተላቸው ስለነበረ ነው" በማለት ይናገራሉ። ኤርትራውያን ተጫዋቾች ለስፖርታዊ ውድድር ከሃገራቸው በወጡ ቁጥር የመጥፋታቸው ነገር እጅጉን እያሳሰበን ነው የሚሉት ሮጀር ሙሊንድዋ፤ "ይህ ከኤርትራም አልፎ ለቀጠናው እግር ኳስ አደጋ ነው" ይላሉ። "እንደ ሴካፋ በኤርትራ እግር ኳስ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አለን። የኤርትራ እግር ኳስ በፍጥነት እያደገ ነው። ከ20 ዓመት የሴካፋ ውድድር ላይ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ሊደረግ በዋዜማ ዕለት ነው 4ቱ ተጫዋቾች የጠፉት። ከዚያም በኬንያ 1 ለ 0 ኤርትራ ተሸነፈች። ልጆቹ ባይጠፉ ኖሮ ውጤቱ ሌላ ሊሆን ይችል ነበር። በአሁኑም የሴካፋ ውድድር የፍጻሜ ተፋላሚዎች ነበሩ። በየግዜው መጥፋታቸው የኤርትራ መንግሥት ከሃገር እንዳይወጡ ያደርጋቸዋል። ይህ ደግሞ የእግር ኳስ ችሎታቸውን እንዳያሳድጉ ያደርጋል" በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ። በየዓመቱ በርካታ ኤርትራውያን ወጣቶች የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ከኤርትራ ወጥተው ይሰደዳሉ። 2016 ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከአፍሪካ ሃገራቸውን ጥለው ከሚወጡ ወጣት አፍሪካውያኖች አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን ናቸው። በኤርትራ ውስን የፖለቲካ ነጻነት እና ማብቂያ የሌለው ብሔራዊ አገልግሎት ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ተደማምሮ ወጣቶች ሃገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እንደሚያደርጋቸው ይነገራል። በጉዳዩ ላይ የኤርትራ የእግር ኳስ ፌደሬሽን አባላት ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
937f288e7c5bd900a0cbd36fe502237d
c528e86b384ef5042150115d145befa7
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላን ወረርሽኝ ለመግታት ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑና በመደበኛነት ወደ ሩዋንዳና ኡጋንዳ ለሚገቡ ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች የኢቦላ ክትባት ልትሰጥ እንደሆነ አስታወቀች።
ኮንጎ ለድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች የኢቦላ ክትባት ልትሰጥ ነው\n• በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ባለሙያዎች ጥቃት ደረሰባቸው • የኢቦላ መከላከያ ክትባት በኮንጎ ሊሰጥ ነው በሩዋንዳ ድንበር ላይ በሚገኘው የኮንጎያዊያን የንግድ ማዕከል' ጎማ' የኢቦላ ኬዝ መገኘቱን በቅርቡ አንድ ሪፖርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነበር ለድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች ትኩረት መሰጠት የተጀመረው። ባለፈው ዓመት ብቻ በኢቦላ ምክንያት በትንሹ 1900 ሰዎች ሕይወት ያለፈባት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ መከላከል አስተባባሪ የሆኑት ጂን ጃኪዩስ ሙየምቤ ከሆነ፤ በሩዋንዳ የሚገኙ የጤና ባለሥልጣናትም ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎችን በተመለከተ ለሚደረገው የክትባት ዘመቻ 100 ሺህ ክትባቶችን ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ የክትባት ዘመቻው መቼ እንደሚጀመር አልታወቀም። • ኢቦላ ወደ ኡጋንዳ እየተዛመተ ነው ዶ/ር ሙየምብ እንዳሉት ለድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎቹ ክትባት ከተሰጠ በኋላ የኢቦላ ታማሚ በተገኘባቸው አካባቢዎች ክትባቱን መስጠት እንደሚጀምሩ የህክምና ቡድኑ አስታውቋል። ዓለም አቀፉን የጤና ድርጅት ጨምሮ ዓለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ክትባት አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረ ሲሆን ክትባቱ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ግርታን ፈጥሮ ነበር። ክትባቱ በጆንሰን እና ጆንሰን የተሰራ ሲሆን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለፈው ዓመት ሲሰጥ ከነበረው ከአንድ የሜርክ ክትባት መጠን የተለየ ነው ተብሏል። በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚዛመቱ ሀሰተኛ መረጃዎችና እምነት ማጣት ሳቢያ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ገትቶታል።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
7bf733113d3392dc2d8fe31bce5ba306
d50e2fec85d16fd05efbaa74cfe9a15f
ምዕራባዊያኑ በትግራይ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ምን መከሩ?
ከእነዚህ መሪዎች መካከል የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንግላ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማኽሮ ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ደግሞ ከአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር አባል የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መምከራቸውን ገልፀዋል። ሚኒስትር ብሊንከን በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀው በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። ጨምረውም በትግራይ ክልል ምንም ዕክል የሌለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍሰት እንዲኖር ጥሩ አቅርበዋል። 'ነገር ግን ተግዳሮቶች ቢኖሩም ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ለውጥ እንዲቀጥልና ሰላማዊ ለውጥ እንዲኖር ድጋፍ እንደምታደርግ' ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ለውጥ ለመደገፍ ላላቸው ቁርጠኝነት አመስግነዋል። አክለው በዩኤስ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚኖር ጠንካራ ግንኙነት ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ አስፈላጊ እንደሆነ አስምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው በፃፉት መልዕክት ትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ ምንም ያሉት ነገር የለም። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀርመኗ መራሂተ መንግሥት ጋር ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ስለሃገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም ስለ ኮቪድ-19 እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነቶች ማውራታቸውን በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። በኢትዮጵያ የጀመርን ኤምባሲ የትዊተር ገፅ በበኩሉ መራሂተ-መንግሥት ሜርክል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶቸና መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቋል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ጋር በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ስለማጠናከር እንዲሁም ሃገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መምከራቸውን አስታውቀዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማኽሮ ስለዚህ ጉዳይ በማሕበራዊ ድር አምባዎቻቸው ያሉት ነገር ባይኖርም የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው መግለጫ ፈረንሳይ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባትና የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ፈቃድ እንዲሰጥ መጠየቋን አስታውቋል። በሌላ በኩል በአስመራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የኤርትራ መንግሥት ወታደሮቹን ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲያስወጣ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች ብሏል። ኤምባሲው በፌስቡክ ገፁ የአሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባን አጋርቷል። በዘገባው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ 'የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ አሜሪካ እንዳላት' ተናግረዋል ብሏል። የኤርትራ መንግሥት በትግራይ ክልል ስላለው ጦርነት ብዙም ያለው ነገር ባይኖርም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት አልተሳተፉም ሲል በተደጋጋሚ አስተባብሏል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ አምባሳደሮች በቅርቡ ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አሳስቦናል ብለው ግልፅ ደብዳቤ ፅፈው ነበር። የኤርትራ መንግሥት ማስታወቂያ ሚኒስትር ለዚህ ግልፅ ደብዳቤ ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
6ec4c83bb69f8f0712490f5baddb59c1
7459f6a60cfc5ecec3142605e99a67ab
‹‹የግጭት አዘጋገብ ጥንቃቄ የተሞላበት ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ
አዲስ አበባ፡- የቃላት አመራረጥ፣ አገላለፅና በአጠ ቃላይ የሚተላለፉ የግጭት ዘገባዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ገለፁ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እናደተናገሩት፤ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ለግጭት መነሳት ብዙ ምክንያቶች ባሉባት አገር የግጭት አዘጋገብ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት። ‹‹መገናኛ ብዙሃን በባህሪያቸው ግጭትን የማምጣት አቅም አላቸው፡፡ ይህ በተለያዩ አገራት ታይቷል፤ ታሪክም መዝግቦታል፡ ፡›› ብለዋል፡፡ እንደዶክተር ጌታቸው ገለፃ፤ አሁን ያለው ግጭት ሁሉም መነሻቸው መገናኛ ብዙሃን ናቸው በሚል በዋነኛ መንስኤነት መጥቀስ ባይቻልም፤ ግጭቶችን ለማብረድ ቀድሞ መንስኤዎችን አጥንቶ ለህብረተሰቡ በማሳወቅ ችግሩን ማስቀረት እንዲቻል ያለውን አቅም ሙሉ ለሙሉ ተጠቅሞ አለመስራት ታይቷል፡፡ አዘጋገብ ላይም ጋዜጠኞቹ ከአገሪቷ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እሳቤ ነፃ ባለመሆናቸው የራሳቸው ሃይማኖት፣ ብሔርና ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ የኔ ከሚሉት አንፃር እየተነሱ የሚዘግቡበት ሁኔታም መኖሩን አመልክተው፤ ነገር ግን በጥንቃቄ መዘገብ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 25/2011
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=10012
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
4af965aa8aba187ff3a1592a5c84cc8e
e87dc704cbd322622be13b09f1d2fa9b
አንደኛው ክንፉ በአየር ላይ የተቦደሰው አውሮፕላን በሰላም አረፈ
ቦይንግ 777 የሆነው አውሮፕላን 231 መንገደኞች ያሳፈረ ሲሆን በተጨማሪ 10 የአየር መንገዱ ሠራተኞች ነበሩ። ምንም እንኳ አውሮፕላኑ በደረሰበት እክል ምክንያት አካላቱ እየተቦዳደሱ ዴንቨር አካባቢ ያሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ቢያርፉም ተመልሶ በሰላም ማረፍ ችሏል። አውሮፕላኑ በደረሰበት አደጋ ምክንያት ምንም ዓይነት ጉዳት ሰው ላይ አለመድረሱ ተዘግቧል። የብሩምፊልድ ፖሊስ ከአውሮፕላኑ የወዳደቁ ናቸው የተባሉ የአንደኛው ሞተር ስብርባሪዎች ከመኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ ማግኘቱን በፎቶ ማስረጃ አረጋግጧል። ተሳፋሪዎች ልክ አውሮፕላኑ እንደተነሳ 'ከባድ ፍንዳታ' መስማታቸውን ተናግረዋል። የበረራ ቁጥሩ 328 የሆነው ይህ አውሮፕላን የዩናይትድ ኤርላይንስ ንብረት ነው። አውሮፕላኑ ከዴንቨር አውሮፕላኑ ማረፊያ ወደ ሆኖሉሉ [ሁዋይ] እየበረረ ሳለ ነው የቀኝ ክንፍ ሞተሩ ላይ አደጋ ያጋጠመው ሲል የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር አሳውቋል። ኤፒ የዜና ወኪል ያነጋገረው አንድ ተሳፋሪ ከባድ ፍንዳታ የተሰማው የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ መልዕክት እያስተላለፈ ሳለ ነው ብሏል። "አውሮፕላኑ በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ፤ ከዚያ የምንበርበት ከፍታ ትተን ወደታች መምዘግዘግ ጀመርን" ሲል ነው ተሳፋሪው ሁኔታውን የገለፀው። ተሳፋሪው አክሎ ምናልባት አደጋ ቢከሰት መለየት እንዲችሉ እሱና ባለቤቱ መታወቂያ ወረቀታቸውን በኪሳቸው እንዳኖሩ ተናግሯል። በይነ መረብ ላይ የተለጠፉ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት እክል ከገጠመበት ክንፍ ላይ ጭስ ሲወጣ ነበር። አንድ አውሮፕላኑ ውስጥ የነበረ ተሳፋሪ የቀረፀው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው አንደኛው ሞተር በእሳት ከተያያዘ በኋላ ተሰብሮ ወደታች ተምዘግዝጓል። ሲኤንኤን ያናገረው አንድ የአካባቢው ነዋሪ የአውሮፕላኑ ስባሪ ከሰማይ ወደታች ሲወድቅ አይቶ ልጆቹን ከለላ ፍለጋ ሲሯሯጥ እንደነበር ተናግሯል። አደጋው የተከሰተው በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ቅዳሜ ከሰዓት 7 ሰዓት አካባቢ ነው። የብሉምፊልድ ፖሊስ ነዋሪዎች የአውሮፕላኑን ስብርባሪ ከቦታው እንዳያነሱ አሳስቧል። የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደርና ብሔራዊው የትራንስፖርቴሽን ሴፍቲ ቦርድ አደጋውን እንደሚያጣሩ ተነግሯል።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
afcb678b3e812428026a89371eff7b66
ae4ecaeb4f65c09159403682a76761a5
ከእሁድ ዕለት መስከረም 18፣2012 ጀምሮ በጎንደር አካባቢ፣ አዘዞና ማራኪ [ቀበሌ 18] አካባቢ፣ በነበረው አለመረጋጋት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
"የሰለጠነና በሙሉ አቅም የሚዋጋ ኃይል ነው ችግሩን የሚፈጥረው" የማዕከላዊ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ\nባለፈው ሳምንት መጨረሻ በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ አካባቢ በተከሰተ ግጭት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን አስከሬን ወደ ጎንደር በሚመጣበት ወቅት፣ ወጣቶች በሁኔታው ተቆጥተው በከተማዋ አንጻራዊ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በጎንደር ነዋሪ የሆኑት አቶ ዘነበ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከእሁድ ጀምሮ ወጣቱ በአዘዞና ቀበሌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ የቅማንት ተወላጆች ላይ ጉዳት የማድረስና ቤታቸውን የማቃጠል እርምጃዎች ተፈፅሟል ይላሉ። • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ • የአማራ ክልል ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር በቁጥጥር ስር ዋሉ • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ ይህም የሆነው ጭልጋ የሞቱ ሰዎች አስከሬን ጎንደር ሲገባ "በግጭቱ ተሳትፎ በሌላቸው የቅማንት ተወላጆች ላይ ወጣቱ የበቀል እርምጃ በመውሰዱ ነው" በማለት ይከስሳሉ። ሌላኛው ስሙን መጥቀስ ያልፈለገው የጎንደር ከተማ ነዋሪ ደግሞ "ወጣቱ በጭልጋ የተገደሉትን ተከትሎ በከተማዋ የሚኖሩ ነገር ግን ይህ ችግር እንዲፈጠር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሰዎች ይያዙልን በማለት ወደ ቤታቸው ሲያመራ ቤታቸው ውስጥ ሆነው ተኩስ ከፍተዋል" ይላል። በዚህም ምክንያት አንድ የልዩ ሃይል አባል እና አንድ ሰላማዊ ግለሰብ ግርግሩን በማረጋጋት ላይ እያሉ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ይናገራል። "ሰዎቹም ሙሉቀን ሲተኩሱ ውለዋል፤ በቂ ትጥቅ የነበራቸውና በኋላም ቤታቸው ሲፈተሽ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎች ተገኝተውባቸዋል" በማለት በቅማንት ተወላጆች ላይ "አንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አልደረሰም" ይላሉ። አቶ ዘነበ እንደሚሉት ግን በተነሳው ግርግር ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል፤ ንብረት ተዘርፏል፤ ቤቶችም ተቃጥለዋል፤ ይህ ጥቃትም "አንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ ነው" ብለዋል። ለዚህ ደግሞ "የመንግሥት እጅ አለበት" ባይ ናቸው። ከጎንደር ከተማ ትንሽ ወጣ ብላ በምትገኘው ቁስቋም አካባቢ ከፍተኛ ቦታ ላይ ሆነው የተኩሱም ድምፁም ጎንደር ስለሚሰማ ሽብር ለመፍጠር እንጂ የተደራጀ ጥቃት አልተሰነዘረም የሚሉት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት ግለሰብ አሁንም በተለያዩ የጎንደር ከተማና ዙሪያዋ አልፎ አልፎ በየግቢያቸው ሆነው የሚተኩሱ አሉ፤ በተወሰነ መልኩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል፣ የትራንስፖርት አገልግሎትም በአንጻሩ ቀንሷል በማለት የዛሬውን የጎንደር ውሎ ይናገራሉ። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩ ገልጸው በአጠቃላይ በከተማዋ ውስጥ የተቃጠለ ቤት አለመኖሩንና አልፎ አልፎ ግን መስኮታቸው የተሰባበሩ ቤቶች እንዳሉ ገልጸዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እንየው በአካባቢው (በማዕከላዊ ዞን) አሁን አንጻራዊ መረጋጋት መኖሩን ገልጸዋል። "በሎጂስቲክስም በአካልም ድጋፍ የሚደረግለት 'ጽንፈኛው ኮሚቴ' ግድያዎችን በመፈጸም ግጭቶችን ወደ ጎንደር ከተማ የማስገባት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል" ብለዋል። ይህንንም ለመከላከል ከተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸው "በተደራጀ፤ በሰለጠነ እና በሙሉ አቅም የሚዋጋ ኃይል ነው ችግሩን የሚፈጥረው" በማለት በህዝብ ላይ ትንኮሳ በመፍጠር ችግሩን በህዝቦች መካከል ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል። "የውክልና ጦርነት አለ የምንለው ዝም ብለን አይደለም" የሚሉት ኮማንደሩ ሌሎች ያሰማሯቸው ኃይሎች ናቸው ያሏቸውን በቀጣዮቹ ጊዜያት "አንድ ሁለት ተብለው በሚቆጠሩ ማስረጃዎች ይፋ እናደርጋለን" ብለዋል።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
0b9ce89d2afa19e3052f8bd9663973ac
91b6fcb2746bcf75e7708044021338e1
በ33 ሚሊዮን ዶላር የብረት ፋብሪካ ተገንብቶ ተመረቀ
በደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች የተቋቋመው ኢኮስ የብረታ ብረት ማምረቻ ኃላፊነቱ የግል ማኅበር፣ በ33 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባው ፋብሪካ በይፋ ተመርቆ ተከፈተ፡፡ኩባንያው በዱከም ከተማ ያስገነባውን ፋብሪካ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲያስመርቅ፣ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ጨምሮ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ኩባንያው የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል ከዓመታት በፊት በራሳቸው አማካይነት በተደረገለት ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ፋብሪካው ተጠናቆ በማየታቸው ደስተኛ እንደሆኑና በመንግሥትም በኩል አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግለት አስታውቀዋል፡፡ኢኮስ ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስዶ መንቀሳቀስ የጀመረ ሲሆን፣ የፋብሪካውን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ጀምሯል፡፡ ኩባንያው በመጀመሪያው የፕሮጀክት ምዕራፍ በዓመት 210 ሺሕ ቶን የግንባታ ብረቶችንና ገመድ ተሸካሚ ምሰሶዎችን የማምረት አቅም እንዳለው ታውቋል፡፡ነገር ግን ኩባንያው አሁን ባለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ ጥሬ ዕቃዎችን ማስገባት ስለማይችል፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት እስከ 15 ሺሕ ቶን ብቻ ለማምረት እንደሚገደድ አስታውቋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግሩ እንደሚፈታ ተስፋ እንዳላቸው የተናገሩት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሼል ሲ.ቾ፣ ችግሩን ለመፍታት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር እየሠሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡በዋናነት የሚያስፈልጉትን የጥሬ ዕቃዎች ከደቡብ ኮሪያ፣ ከዩክሬንና ከቱርክ ኩባንያዎች እየተረከበ የሚገኘው ኩባንያው፣ በሙሉ አቅም ማምረት ሲጀምር የምርቱን መጠን እንደሚጨምር ተገልጿል፡፡ በሁለተኛ ምዕራፍ የግንባታ ፕሮጀክቱ በዓመት 500 ሺሕ ቶን የአርማታ ብረትና የተለያዩ የብረታ ብረት ምርቶችን ለማምረት የሚያገለግለውን የቢሌት ጥሬ ዕቃ የሚያመርት ፋብሪካ የመክፈት ዕቅድ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡በዓመት እስከ 200 ሺሕ ቶን የሚሆኑ ውድቅዳቂ ብረቶችን ከአገር ውስጥ በመሰብሰብ እንደ ጥሬ ዕቃ ለመጠቀም ኩባንያቸው ዕቅድ እንዳለው፣ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናግረዋል፡፡ይህ ፕሮጀክት እንደ ዕቅዱ ስኬታማ ከሆነ መንግሥት በዓመት ለብረታ ብረት ጥሬ ዕቃዎች ከሚያወጣው ከፍተኛ ወጪ እስከ 50 ሚሊዮን ዶላር ያድናል ተብሏል፡፡በአሁኑ ወቅት 14 ያህል የአርማታ ብረት አምራቾች በሥራ ያሉ ሲሆን፣ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ መንግሥት የአገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት የተለያዩ የቀረጥና የታክስ እገዛዎች ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ አምራቾቹ ያላቸውን አቅም ገንብተው የአገር ውስጥ ገበያውን እንዲቆጣጠሩና ከውጭ የሚመጣውን ብረት እንዲተኩ ቢጠበቅም፣ አሁንም ከፍተኛ መጠን ያለው የብረት ጥሬ ዕቃ በውጭ ምንዛሪ እየተገዛ ወደ አገር ውስጥ እየገባ ነው፡፡የብረት አምራቾቹም የሚያስፈልጉዋቸውን ጥሬ ዕቃዎች ማለትም የወዳደቁ ብረቶችን ከአገር ውስጥ ተጠቅመው እንዲያመርቱ ቢጠበቅም፣ አሁንም በተለያዩ ምክንያቶች የወዳደቁ ብረቶችን በብዛትና በጥራት ማግኘት አዳጋች መሆኑ ይነገራል፡፡በዚህም ምክንያት የአገሪቱ ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ለብረታ ብረት  ጥሬ ዕቃዎች ግዥ እየወጣ ነው፡፡
3ቢዝነስ
https://www.ethiopianreporter.com/article/13393
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ffd5a8859660a63db430b144d52f64c0
335209812e84462c654dd09a883cf25c
ካሜሩን ጋናን 2 ለ 0 አሸንፈች
በጋቦን አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ለፍፃሜ የሚጋጠሙት ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ ታውቀዋል፡፡ካሜሩን ጋናን 2 ለ 0 አሸንፋ ትናንት ቡሩኪና ፋሶን 4 ለ 3 ከሸኘው የግብፅ ቡድን ጋር ለዋንጫው ፍፃሜ ትጋጠማለች፡፡ለደረጃ ቅዳሜ ቡሩኪናና ጋና ይጫወታሉ፡፡በዛሬው ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ብልጫ ያሳየውና ሁለት ድንቅ ጎሎችን ያስቆጠረው የካሜሩን ቡድን ነው፡፡የፍፃሜ ግጥሚያዎች የሚካሄዱት በዋናዋ ከታማ ስቴዲየም ይሆናል፡፡
4ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/african-cup-of-nations-2-2-2017/3703910.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3268bec5eaf42514edc851784e0ed557
5711e5df462c89a86f60459214293a46
ጥራቱን ያልጠበቀ የጨው ምርት ገበያውን ማጥለቅለቁ ጥያቄ አስነስቷል
የምርት ጥራት ደረጃውን ያልጠበቀ፣ የአዮዲን ይዘቱ አነስተኛ የሆነና ከነአካቴው አዮዲን የሌለው የጨው ምርት ከአፋር ክልል አፍዴራ ወደ መሀል አገር ገበያ በብዛት እየባ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ ይህም ድርጊት ጥያቄ አስነስቷል፡፡ለአገሪቱ ለምግብ ፍጆታ የሚውለው ጨው በአብዛኛው የሚመረተው በአፋር ክልላዊ መንግሥት አፍዴራ ሐይቅ በባህላዊ ጨው አምራቾች ማኅበር ነው፡፡ የአገሪቱ ወርኃዊ የጨው ፍጆታ 360,000 ኩንታል ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 310,000 ኩንታል የሚሆነው በአፍዴራ በባህላዊ መንገድ እየተመረተ በጨው ነጋዴዎች አማካይነት ለማዕከላዊ ገበያ ብሎም በመላ አገሪቱ ይከፋፈላል፡፡ ጨው ለሰው ልጆች ጤና አስፈላጊ የሆነውን አዮዲን የተሰኘውን ንጥረ ነገር ሊኖረው የሚገባ በመሆኑ ለምግብነት የሚውል ጨው ከአዮዲን ጋር እንዲደባለቅ ይደረጋል፡፡ አዮዲን ለሕፃናት አዕምሮ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ የአዮዲን እጥረት የአዕምሮ ዝግመት፣ የእንቅርት በሽታንና ውርጃን እንደሚያስከትል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡መንግሥት ለምግብነት የሚውል የጨው ምርት ከአዮዲን ጋር እንዲደባለቅ የሚያስገድድ ሕግ አውጥቷል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሕፃናት መርጃ ድርጅት ጋር በመተባበር ባህላዊ የጨው አምራቾች ማኅበራት አቅማቸውን እንዲገነቡና የአዮዲን ንጥረ ነገር በምርታቸው ውስጥ እንዲጨምሩ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡መጋቢት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. የሚኒስትሮች ምክር ቤት የምግብ ጨው አዮዲን እንዲኖረው የሚያስገድድ ደንብ አውጥቷል፡፡ ደንቡ ማንኛውም ሰው አዮዲን የሌለው ጨው ለሰው ምግብነት አገልግሎት እንዲውል ማዘጋጀት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከማቸት፣ ማከፋፈል፣ ማጓጓዝ ወይም መሸጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ ማንኛውም ለሰው ምግብነት የሚውል አዮዲን ያለው ጨው አግባብ ባለው አካል በሚያወጣው የጨው ደረጃዎች መሠረት የጥራት ደረጃ መመዘኛ ማሟላት እንዳለበት ይጠቅሳል፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው ይህን ደንብ ወይም ደንቡን ለማስፈጸም የወጡትን መመርያዎች ተላልፎ ቢገኝ አግባብ ባላቸው የአዋጅ ድንጋጌዎች መሠረት ይቀጣል፤›› ይላል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ፡፡ይህን ደንብ የማስፈጸም ሥልጣን በአዋጅ የተሰጠው የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአገሪቱን ሕግ በመተላለፍ የጥራት ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ዝቅተኛ የአዮዲን ይዘት ያለው ወይም ከነጭራሹ አዮዲን የሌለው የምግብ ጨው ለገበያ እየቀረበ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአፍዴራ የሚገኙ የጨው አምራቾች ማኅበራት የአመራረት ጥራት ብቃት ላይ የሚነሳው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከነአካቴው አዮዲን ያልተቀላቀለበት የጨው ምርት በስፋት ወደ ገበያ እየገባ እንደሆነ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ለኅብረተሰቡ አዮዲን የሌለው ጨው እየቀረበለት ነው፡፡ ልጆቻችንን አዮዲን የሌለው ጨው እየመገብን ሊሆን ይችላል፡፡ ጉዳዩ እንደ አገር አሳሳቢ ነው፤›› ብለዋል ምንጮች፡፡ እንደ ማሳያ የሚጠቅሱት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጨው የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰመራ ከተማ ኬላ በኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን መያዛቸውን ነው፡፡ባለፈው ሳምንት ባለሥልጣኑ ደረጃውን ያልጠበቀ የጨው ምርት የጫኑ 40 ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ጉዳዩ ያሳሰበው የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን በአፋር ክልል በሚገኙ መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ የሚያደርገውን የጨው ምርት ጥራት ቁጥጥር ማጠናከሩን አስታውቋል፡፡ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አብረሃም መሥሪያ ቤታቸው በጥራት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሆነ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በአፍዴራና በሌሎችም ጣቢያዎች ያሰማራቸው ኢንስፔክተሮች ፈጣን የመመርመሪያ መሣሪያ እንዳላቸውና ጥብቅ ፍተሻ እንደሚያደርጉ አቶ ሳምሶን ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹አዮዲን ያልተቀላቀለበት ጨው ለኅብረተሰቡ ፍጆታ እንዲውል ለሽያጭ ሊያቀርቡ ሲሉ እየተያዙ ነው፤›› ብለዋል፡፡ጨው የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከላይ የተጫኑት ጆንያዎች አዮዲን ያለው ጨው የያዙ ሆነው ከታች ግን አዮዲን ያልተቀላቀለበት ጨው የያዙ ጆንያዎች ተጭነው እንደተገኙ አስረድተዋል፡፡ ለፋብሪካዎች በግብዓትነት የሚቀርበው ጨው አዮዲን ያልተደባለቀ እንደሆነ፣ አምራቾችና ነጋዴዎች ለፋብሪካዎች አዮዲን የሌለው ጨው ማቅረብ እንደሚችሉ የገለጹት አቶ ሳምሶን፣ ይህን ለማድረግ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የድጋፍ ደብዳቤውን በፍተሻ ኬላዎች ላይ እያሳዩ ለፋብሪካዎች ምርታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ይሁን እንጂ ለፋብሪካ በጥሬ ዕቃነት የሚቀርብ በማስመሰል ለምግብነት ፍጆታ የሚውል ጨው (አዮዲን የሌለው) ለገበያ ለማቅረብ ጥረት ሲደረግ እየተያዘ እንደሆነ አቶ ሳምሶን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ይህን ችግር ለመፍታት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከንግድ ሚኒስቴርና ከሌሎች የዘርፉ መሥሪያ ቤቶች ጋር ሆነን የመቆጣጠር ሥራ እያከናወንን ነው፤›› ብለዋል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት 40 ተሽከርካሪዎችም አስፈላጊው የምርመራ ሥራ ተካሂዶ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ባህላዊ የጨው አምራቾች ጨውን ከአዮዲን ጋር የሚያደባልቁበት መንገድ ነው፡፡ አምራቾቹ አዮዲኑን በጨው ላይ በነሲብ የሚረጩት በመሆኑ አዮዲኑ ከጨው ጋር በአግባቡ በሚፈለገው መጠን አይዳረስም፡፡‹‹በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ጨው የማቀላቀል ሁኔታ ላይ ችግር ይከሰታል፡፡ የአዮዲን ይዘት የማነስና የመብዛት ሁኔታዎች እንዳሉ በቁጥጥር ሥራ ወቅት አይተናል፤›› ብለዋል አቶ ሳምሶን፡፡አዮዲን ለጤና አስፈላጊ የመሆኑን ያህል ከሚፈለገው (በደረጃ ከተቀመጠው) መጠን በላይ ሲገኝ ደግሞ ለሰውነት መርዛማ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ዘመናዊ የገበታ ጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ ባለሙያዎቹ ይመክራሉ፡፡በባህላዊ አምራቾች በኩል የታየውን አዮዲን የመቀላቀል ድክመት ለማረም የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ከሕፃናት መርጃ ድርጅትና ማይክሮ ኒዩትረንት ኢንሼቲቭ ተራድኦ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ባህላዊ የጨው አምራቾች ማኅበራት የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር ሆነን ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየሠራን ነው፡፡ ነገር ግን የአዮዲን መጠኑ ከፍና ዝቅ የማለት ሁኔታ አሁንም እያየን ነው፤›› ብለዋል፡፡በተቻለ መጠን አዮዲን የተቀላቀለበት ምርት እንዲያቀርብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ፣ ይህን ለማረጋገጥ በመግቢያና በመውጪያ ኬላዎች በመሣሪያዎች የታገዙ ጥብቅ ፍተሻ በማድረግ ላይ መሆኑን ባለሥልጣኑ ይገልጻል፡፡ የጨው ምርት ዋና ሥራ በሚካሄድበት አፍዴራ ባለሥልጣኑ ክትትል ያደርጋል ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ሳምሶን፣ በአፍዴራ የጨው ምርት ሒደት ላይና የማከማቸት ሒደት ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡‹‹የምርት ሒደት እናያለን፡፡ አዮዲን እንዴት እንደሚቀላቅሉ ከደኅንነት አኳያ እናያለን፡፡ ምርቱን እንዴት እንደሚያከማቹ እናያለን፡፡ ነገር ግን ቁጥጥራችን የተሟላ ነው ማለት አይቻልም፡፡ እኛ እያንዳንዱ ምርት ላይ በየጊዜው በየሰዓቱ እዚያው ቆይተን መመርመር አንችልም፡፡ ያን ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን በተወሰነ ጊዜ የፍተሻ ሥራ እንሠራለን፤›› ብለዋል፡፡ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ማኅበራቱ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ከክልሉ መንግሥት ጋር የተለያዩ ውይይቶች እየተካሄዱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ‹‹የእኛ ሚና አዮዲን የተቀላቀለበት ጨው አስመልክቶ በወጡ ደንቦች ላይ ማብራሪያ መስጠት፣ የተመጠነ የአዮዲን ይዘት የሌለው ጨው የሚፈጥረውን ጉዳቶች ማስረዳት፣ በምርት ሒደትና በአከመቻቸት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ማድረግ፣ የአቅም ችግር ካለ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ መስጠት ነው፤›› ብለዋል፡፡ዘመናዊ የገበታ ጨው ማምረቻ ፋብሪካዎች መቋቋም እንደሚበረታታ የገለጹት አቶ ሳምሶን የጨው ጥራትን ከፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ከጥራት ባሻገር በጨው ምርትና ንግድ ዙሪያ ያለው ሥጋት ከገበያው ፍላጎት በላይ የማምረት ጉዳይ ነው፡፡ በአፍዴራ ሐይቅ ዙሪያ በርካታ የጨው አምራች ማኅበሮችንና ነጋዴዎች የሚገኙ ሲሆን፣ በሚደረገው የገበያ ሽሚያ ከአገሪቱ ዓመታዊ የጨው ፍጆታ በላይ ከሐይቁ እየተመረተ ጥቅም ላይ ሳይውል በሐይቁ አቅራቢያ ተከማችቶ እንደሚታይ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡አላቂ የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ ጉዳዩ አሳሳቢ ነው፡፡ ፌዴራል መንግሥት ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ለጉዳዩ እልባት ሊያበጅለት ይገባዋል ብለዋል፡፡ በአማካይ 25 ሜትር ጥልቀት ያለው የአፍዴራ ሐይቅ በ116.8 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ የተንጣለለ ነው፡፡ በሐይቁ ውስጥ የሚገኘው የጨው ክምችት 290 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ይገመታል፡፡ 
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8C%A5%E1%88%AB%E1%89%B1%E1%8A%95-%E1%8B%AB%E1%88%8D%E1%8C%A0%E1%89%A0%E1%89%80-%E1%8B%A8%E1%8C%A8%E1%8B%8D-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8C%88%E1%89%A0%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%88%9B%E1%8C%A5%E1%88%88%E1%89%85%E1%88%88%E1%89%81-%E1%8C%A5%E1%8B%AB%E1%89%84-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8A%90%E1%88%B5%E1%89%B7%E1%88%8D
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
98d54806b44e6029d3cadf45f04b45bf
7c06c6b4d137d5f72c4deb3e67769d30
የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን የተሰሩ ሥራዎችን ገምግሟል፡፡
የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን የተሰሩ ሥራዎችን ገምግሟል፡፡ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ኮሚሽን የኢኮኖሚ ፣ የሳይንስ ፣ የቴክኒክ እና የንግድ ትብብር ግምገማ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡በጋራ የኮሚሽኑ ግምገማ ላይ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ፣ የትምህርት ሚኒስትር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ. ር) እና የሩሲያ ፌዴሬሽን የተፈጥሮ ሀብቶች እና የአካባቢ ጥበቃ ሚክትል ሚኒስትር እና የፌዴራል የማዕድን ሀብቶች ኤጀንሲ ኃላፊ ሚስተር ኤቭጂኒ ኪሴሌቭ ተሳትፈዋል፡፡በውይይቱ በኮሚሽኑ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ፕሮቶኮል ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች አፈፃፀም ተገምግሟል ፡፡ግብርና፣ ኢነርጂ ፣ ጂኦሎጂ፣ ትምህርት፣ ስፔስ ሳይንስን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የኢትዮጵያ ሩሲያ ትብብር ላይ ሀሳቦች ተለዋወጠዋል፡፡በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት እና በሩሲያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡
4ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.amharaweb.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae-%e1%88%a9%e1%88%b2%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8c%8b%e1%88%ab-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%88%a9-%e1%88%a5%e1%88%ab%e1%8b%8e/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
6be110a801fe912e9dae22d6ad7849d0
4e3193682e74bafd1b18b99b46cb8afd
አፍሪካዊቷ አገር ማዳጋስካር ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ አገር በቀል የሆነ ተክልን በመጠቀም ለኮሮረናቫይረስ የሚሆን መድኃኒት ማግኘቷን ካስታወቀች በኋላ የዓለምን ትኩረት መሳብ ችላ ነበር።
ኮሮናቫይረስ፡ መድኃኒት ነው ስለሚባልለት ተክል ምን ያህል እናውቃለን?\nአርትሚዝያ የተባለውና ከአርቲ ጋር የሚመሳሰለው ተክልን በመጠቀም የተሰራው የሚጠጣ 'መድኃኒት' በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አንድሬይ ራጆሊና ሲሞካሽ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በዋነኛነት የወባ በሽታን ለማከም ጥቅም ላይ ከሚውለው አርትሚዝያ ተክል የሚሰራው 'መድኃኒት' በትክክል ኮቪድ-19ኝን እንደሚያድን በሳይንሳዊ መንገድ እስካሁን አልተረጋገጠም ሲል ቆይቷል። ለመሆኑ ስለዚህ ተክል ባህሪዎችና አጠቃላይ ሁኔታ ምን ያክል እናውቃለን? አርትሚዝያ ከየት መጣ? አርትሚዝያ ዋናው መገኛው ከወደ እሲያ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን በመላው ዓለም በሚገኙኛ ፀሐያማና ሞቃታማ የአየር ጸባይ ባላቸው አገራት በብዛት ይታያል። በዋነኛነት ተክሉ ቻይና ውስጥ ላለፉት 2 ሺህ ዓመታት ለባህላዊ መድኃኒትነት ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። በዚህም እንደ ወባ፣ ትኩሳትና ሌሎች ህመሞችን ለማከም ያገለግል ነበር። ይህ ተክል በቻይናውያን ዘንድ 'ኪንጋኦ' ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከመድኃኒትነት በተጨማሪ አርትሚዝያ የአልኮል መጠጦችም ውስጥ ይጨመራል። የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት ከአርቲ የተሰራውን ጭማቂ ይዘው አርትሚዝያ ኮቪድ-19ኝን ያክም ይሆን? የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት አንድሬይ ራጆሊና ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ ከአርትሚዝያ የተሰራው የሚጠጣ 'መድኃኒት' ላይ ሙከራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በመግለጽ 'መድኃኒቱ' ኮቪድ-19ኝን ለማከም መዋል እንደሚችል ደርሰንበታል ብለዋል። በያዝነው የፈረንጆቹ መስከረም ወርም ቢሆን ይህንኑ አስተያየታቸውን ደግመውታል። ነገር ግን በይፋ ሊታይ የሚችል ማረጋገጫ እስካሁን ድረስ ማዳጋስካር ማቅረብ አልቻለችም። በተጨማሪም 'መድኃኒቱን' ለመስራት ምን አይነት ሂደት እንደተከተሉና ተክሉ ምን ያህል ጥቅም ላይ እንደዋለ የተገለጸ ነገር አለመኖሩ በርካቶች ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። ማዳጋስካር ግን እነዚህን ሁሉ አስተያየቶች ወደጎን በማለት እንደውም ይህንኑ ተክል በመጠቀም ለኮቪድ-19 የሚሆን የሚዋጥ መድኃኒት ማምረት የጀመረች ሲሆን በመርፌ መልክ የሚሰጥ መድኃኒትም በማዘጋጀት ላይ ናት። ለእነዚህ 'መድኃኒቶች' ደግሞ ክሊኒካዊ ሙከራዋን አጠናክራ መቀጠሏን ማዳጋስካር አስታውቃለች። የጀርመን እና የዴንማርክ ተመራማሪዎች ደግሞ አርትሚዝያ ምን ያክል ውጤታማ ሊሆን ይችላል የሚለውን እና እውን ኮቪድ-19ኝን ማከም ይችላል የሚለውን ለማረጋገጥ ጥናት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። አዲስ በሰሩት ጥናትም ተክሉ ኮቪድ-19ኝን የማዳከም አቅም እንዳለው ላቦራቶሪ ውስጥ ማረጋገጥ እንደቻሉ ገልጸዋል። ምንም እንኳን የተመራማሪዎቹ ጥናት በገለልተኛ ባለሙያዎች ባይገመገምም ከተክሉ የተወሰደው ቅንጣት የቫይረሱን እንቅስቃሴ መግታትና ማቀዝቀዝና ኃይለኛቱን መቀነስ እንደሚችል ተገልጿል። ተመራማሪዎቹ በአሜሪካው ኬንተኪ ዩኒቨርሲቲ ስር ሆነው የሚሰሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ክሊኒካዊ ሙከራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። ቻይናም ብትሆን በዚሁ ተክል ላይ ምርምሮችን ማድረግ እንደጀመረች አስታውቃለች። በባህላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ተክል በዘመናዊ ምርምርና እውቅት በመደገፍ የሚደረገው ለኮሮናቫይረስ ፍቱን መድኃኒት የማግኘት ሥራም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎችም ቢሆኑ አርትሚዝያ ኮቪድ-19ኝን ምን ያክል ማከም ይችላል የሚለውን ማወቅ በማሰብ በላብራቶሪ ምርምር ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች። የዓለም ጤና ድርጅት ግን አሁንም ቢሆን ከአርትሚዝያ ስለተሰራው 'መድኃኒት' ከማደዳስካር የተብራራ መረጃ አላገኘሁም እያለ ነው። የድርጅቱ የአፍሪካ አማካሪ ዢን ባፕቲስት ኒኬማ ለቢቢሲ እንደገለጹት ድርጅቱ በሚያገኘው መረጃ ላይ በመመስረት ክሊኒካል ሙከራዎች ላይ...
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
4941575f07ee7ff5e16cd705d9ca2ae2
20a763fc75ce0691eae3aaf5202902ea
ከቻይና የመጡ አራት ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ስለመሆናቸው እየተጣራ ነው
በቻይና ኩቤት ግዛት ውሃን (Wuhan) ከተማ ውስጥ ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ አራት ተማሪዎች በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው፣ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በሚገኘው ልየታ ማዕከል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር) ማክሰኞ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ተጠርጣሪዎቹ በልየታ ማዕከል ክትትል እንዲደረግላቸው ያስፈለገው ከመካከላቸው አንደኛው ተጠርጣሪ ጉንፋን መሰል ምልክት ስለታየበት ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን በአሁኑ ጊዜ የአራቱም ተጠርጣሪዎቹ ጤንነት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ተሠርቶላቸው ለጉንፋን መሰል በሽታ ኔጌቲቭ መሆናቸው እንደተረጋገጠ፣ ይህም ውጤት ለከፍተኛ ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደተላከ አስረድተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከቻይና ጓንዡ ግዛት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሁለት ቻይናውያን መንገደኞች በአውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የምርመራ ቦታ ለሁለት ሰዓታት ያህል አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ፣ ቫይረሱ ካሉበት አካባቢ ጋር ምንም ግንኙነት ስለሌላቸውና በሙቀት ልየታ መሣሪያውም የተገኘ ምልክት ስለሌለ፣ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጾ፣ በመንገደኞቹ ላይ የማጣራት ሥራ የተከናወነው በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ በሰጠው ጥቆማ መሠረት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተገኘው መረጃ ለመረዳት እንደተቻለው፣ የቫይረሱ መነሻ በሆነው ውሃን ከተማ ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን ትምህርታቸውን ይከታተላሉ፡፡ በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ ለማድረግ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተኛ ክትትልና ጥንቃቄ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡እንደ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኤባ (ዶ/ር) ማብራሪያ ከሆነ፣ በውሃን ከተማ የተከሰተውና ኖቭል ኮሮና ቫይረስ 2019 በሚል ስያሜ የሚጠራው ይህ በሽታ፣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ አስፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ እስካሁንም በተካሄደው እንቅስቃሴ ስለበሽታው መረጃ መስጠትና በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ለሁሉም መንገደኞች የሰውነት ሙቀት ልየታ ሥራ መጀመር ይገኝበታል፡፡ የሙቀት ልየታ ሥራ የተጀመረው በዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሐሳብ መሠረት ሲሆን፣ በሙቀቱ መለየት ሥራ ላይ እስካሁን ያጋጠመ ችግር እንደሌለና መረጃ የመስጠቱም ተግባር የሚካሄደው በማንኛውም አየር መንገድ በኩል የሚጓዙ መንገደኞች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ እንደሆነ፣ ከዚህም በተጨማሪ ኢንስቲትዩቱ ለክልሎችና ለባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን የዝግጅት ሥራዎች እንዲያከናውኑ የቅድመ ዝግጅት መልዕክት እንዳሠራጩ ነው የተናገሩት፡፡ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገሮች ጋር የአየርና የየብስ ትራንስፖርት ትስስር የምታደርግ በመሆኑ፣ በሽታውን ሪፖርት ካደረጉት አገሮች ጋርም በአየር መንገዷ አማካይነት በርካታ በረራዎች አሏት፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና ብቻ በአምስት መዳረሻዎች ማለትም ቤጂንግ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ሻንግሃይ፣ ቸንዱና ጓንዡ በረራዎችን ያደርጋል፡፡ በዚህም የተነሳ ቫይረሱ የሚገባባቸው ዕድሎች ሰፊ እንደሆነ ነው የጠቆሙት፡፡ በሽታው ወይም ወረርሽኙ ያለባቸው ሰዎች ድንገት ቢገኙና ተጨማሪ ምርመራና መታየት የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጊዜያዊ የማቆያ ማዕከል ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ቦታ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሐኪሞች እንደተመደቡ ተገልጿል፡፡ ለረዥም ጊዜ እየታዩ መታከም የሚያስፈልጋቸው በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታልና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን፣ ከኤባ (ዶ/ር) ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡ በሽታው በጠናባቸው ታማሚዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳንባ ምች (ኒሞኒያ)፣ ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም የሚያሳይ ሲሆን፣ የኩላሊት ሥራን ማቆም ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡ በሽታው ባልበሰሉ ምግቦች፣ በሳልና በማስነጠስ ወቅትና ከታማሚ ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ፣ ባልታጠበ እጅና በመሳሰሉት ይተላለፋል፡፡ በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሮች የሚጓዙ መንገደኞት እጅን በሳሙናና በ መታጠብ አለባቸው፡፡ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ አለመፍጠር፣ ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣ በሕይወት ካሉም ሆነ ከሞቱ ከቤትና ከዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ፣ ከኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከሕክምና ተቋማት፣ ከጉዞ ማኅበራት፣ ከአየር መንገድ፣ ከመዳረሻ ቦታዎች ወይም ከሌሎች የጤና መረጃ ምንጮች ስለበሽታው በቂ መረጃ ማግኘትና ራሳቸውን ከበሽታው መከላከል እንደሚጠበቅባቸውም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ 2019 በሚል ስያሜ የሚጠራው በሽታ ከታኅሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና ውሃን ከተማ መከሰቱን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ በዚሁ በሽታ በቻይና 106 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል፡፡ ሌሎች 400 ያህል ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተጠቅተው በከፋ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ከ5,700 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ በበሽታው ተይዘው የነበሩ 51 ሰዎች በተደረገላቸው ሕክምና አገግመው ተነስተዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ ባሉ እንደ አሜሪካ፣ ታይላንድ፣ አውስትራሊያ፣ ሲንጋፖር፣ ደቡብ ኮሪያ ከቻይና በተነሱ መንገደኞች አማካይነት መሠራጨቱን ዘገባዎች ጠቁመው፣ በእነዚህም የሞተ ሰው ባይኖርም እንኳን 44 የሚደርሱ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆናቸው ታውቋል፡፡
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.ethiopianreporter.com/article/17947
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3c3b4c63d7096a1668060a9c5e978def
34ca8bb5724de3a60ca603a31a95d8c5
ከዛሬ 42 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ጦር የሶማሊያን ጦር አሽንፎ ካራማራ ላይ ስንደቅ አላማውን አውለበለበ
ከዛሬ 42 ዓመታት በፊት የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ገብቶ የነበረውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማስወጣት ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማወለብለቡን ታሪክ ያስታውሳል፡፡ የካራማራ ድል ከደርግ ውድቀት በኋላ በመንግስት ደረጃ የማይከበር ድል ቢሆንም የቀድሞ ሰራዊት አባላትና ግለሰቦች በተነሳሽነት እያከበሩት ነው፤ በዓሉም ብሄራዊ በዓል ሆኖ በመንግስት እንዲከበር ይፈልጋሉ፡፡ ሶማሊያ በ1952 ዓ.ም ከጣሊያንና ከእንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ነፃነቷን ባገኘች ማግሥት የሀገሪቱ መሪዎች “ታላቋ ሶማሊያን እንገነባለን” የሚል ህልም ማለም ጀመሩ፡፡ በዚህም ምክንያት በ1953 ዓ.ም የድንበር ላይ ትንኮሳ ጀምረው በ1956 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብድረሺ አሊ ሸርማርኬ እንዲሁም በ1969፣ በ1972 እና በ1973 ዓ.ም ደግሞ ፕሬዝደንት ዚያድ ባሬ (ሜጀር ጀኔራል) የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ እንዲገባና ወረራ እንዲፈፅም ሰራዊታቸውን አዘዙ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ደግሞ ሰርጎ ገቦችን አስታጥቆ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በማስገባት ፈንጅ በማፈንዳት፣ ድንገተኛና የደፈጣ ጥቃቶችን በመፈፀም እንዲሁም ባለስልጣናትንና ሰላማዊ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት መሰናክል ሆነው መቆየታቸውንም በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪዎች ይገልጻሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የሶማሊያ ወረራዎችና ጥቃቶች በኢትዮጵያ አሸናፊነት ቢመለሱም ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን አለመቻሉ ይገለጻል፡፡ በተለይ የ1969 ዓ.ም የዚያድ ባሬ ወረራ የኢትዮጵያ ድንበር በምስራቅ በኩል እስከ 700 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በደቡብ በኩል ደግሞ እስከ 300 ኪሎ ሜትር በሶማሊያ ሰራዊት እንዲደፈር፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዲሞቱና እንዲቆስሉ፣ አካል ጉዳተኛ እንዲሆኑ በአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በርካታ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ያደረገ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በወቅቱ በብዙ የውስጥ ችግሮች (የመሐል አገር የሥልጣን ሽኩቻ፣ የነጻነት ጠያቂዎች በሃገር ቤት፣ የተለመደው ድህነትና ረሀብ …) ተወጥራ ስለነበር የዚያድ ባሬ ወረራ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባት ነበር ይላሉ የታሪክ ጸሐፊያን፡፡ ሶማሊያ ኢትዮጵያን ለመውረር ሰፊ የሰው ኃይል፣ የትጥቅ፣ የስንቅ፣ የሥነ ልቦና ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች፤ኢትዮጵያ ግን በውስጣዊ ችግሮች ከመወጠሯም ባሻገር በወቅቱ የነበራት የሰራዊት ቁጥርና ጥራትእንዲሁም የትጥቅ አቅርቦት እጅግ የተመናመነ እንደነበርም ነው የሚገለጸው፡፡300ሺ የሚሆን ሕዝባዊ ሰራዊት በአጭር ጊዜ ሰልጥኖ ለውጊያ የተሰለፈ ሲሆን ፤የኩባና የደቡብ የመን መንግሥታት ጦራቸውን ይዘው ከኢትዮጵያ ጎን መሰለፋቸውም ይታወሳል፡፡ ሶቭየት ኅብረት በጀኔራል ፔትሮቭ የሚመሩ ወታደራዊ አማካሪዎቿን ለኢትዮጵያ ረዳት አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ መላኳንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከኢትዮጵያ በኩል ተሰልፈው ህይወታቸውን ላጡ ኩባውያ ወታደሮች በአዲስ አባበ መታሰቢያ ተሰርቶላቸዋል፡፡  የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት የማባረሩ ዘመቻ በሐምሌ ወር 1969 ዓ.ም ተጀመረ፡፡ ኢትዮጵያውያን በምድርና በአየር አስደናቂ ገድል ስለመፈጸማቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ተናግረዋል፡፡ ዘመቻው እስከ የካቲት ወር 1970 ዓ.ም ቆይቶ የሶማሊያ ጦር በኢትዮጵያ ሰራዊት ተከቦ መፈናፈኛ ሲያጣ ለአሜሪካና ለሶቭየት ኅብረት የድረሱልኝ ጩኸቱን አሰማ፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሶማሊያን ጦር እያባረረ የሶማሊያን ድንበር ጥሶ ወደ ሃርጌሳ ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት ስለነበር ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው የነበሩት የውጭ አገራት የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳይገባ ልመናና ተማፅኖ ጭምር ማቅረብ ጀመሩ፡፡ አሜሪካና ሶቭየት ኅብረትም ኢትዮጵያና ሶማሊያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ፤የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ሶማሊያ ድንበር ጥሶ እንዳይገባና የሶማሊያ ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር በ24 ሰዓታት ውስጥ ጠቅልሎ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የአሜሪካና የሶቭየት ኅብረት ጥሪ ተፈፃሚ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ሰራዊትም የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለበ፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህ የድል ዕለት ታዲያ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው አይደለም የሚሉ ወቀሳዎች አሉ፡፡በተለይ ዕለቱን ሳይቀር ብዙዎች የማያስታውሱት እንደሆነና መንግስትም ሰፊ ትኩረት እየሰጠው እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ በወቅቱ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪዎች ሳይቀሩ እየተዘከሩና እየታወሱ አለመሆኑም ይገለጻል፡፡ 42ኛው የካራማራ ድል በቀድሞው የሰራዊት መሪዎችና አባላት፣ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር እንዲሁም ግለሰቦች በግል ተነሳሽነት አክብረውታል፡፡
5ፖለቲካ
https://am.al-ain.com/article/42-years-ago-today-ethiopian-army-managed-to-defeat-aggressor-somalia
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
905833e5fd32ca7a29ae1087f3f8da28
fb5ab11908f55a78e6c94a5488d229f8
ግብፅ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀመረች
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2006 (ዋኢማ) – የግብፅ መንግሥት በታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ በተመለከተ ሱዳን ለኢትዮጵያ የሰጠችውን ድጋፍ ለማጨናገፍ፣ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ መጀመርዋን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡የተለያዩ የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ሰሞኑን እንደዘገቡት፣ የግብፅ መንግሥት የተለያዩ የመንግሥት አመራሮችና ፖለቲከኞች ከሱዳን መንግሥት አቻዎቻቸው ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል፡፡ለአብነት ከተጠቀሱት መካከል የግብፅ አል ዋፍድ ፓርቲ ሊቀመንበር ሳይድ አል ባዳዊ በካይሮ ከሱዳን አምባሳደር ከማል ሐሰን ዓሊ ጋር በሁለቱ አገሮች ድንበር የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በዋነኝነት መክረዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች ድንበር የጦር መሣሪያ ዝውውር ለማስቆም የተነጋገሩት ሁለቱ ባለሥልጣናት፣ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው የታላቁ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብና በሱዳን አቋም ላይ ተነጋግረዋል፡፡ከውይይታቸው በኋላ አል ባዳዊ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላት አቋም ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ነው መባሉ በእውነት ላይ ያልተመሠረተ ተባራሪ ወሬ ነው ብለዋል፡፡ በግድቡ ላይ ሦስቱ አገሮች ጥልቅ ውይይት አካሂደው የሁሉንም ወገን ጥያቄዎች በሚመለስ ደረጃ መግባባት ይኖርባቸዋል የሚሉት አል ባዳዊ፣ ሱዳን የግብፅን የውኃ ፍላጐት በሚነካና ብሔራዊ ደኅንነቷን በሚጐዳ ጉዳይ ላይ አሉታዊ አቋም አትይዝም ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ የሱዳን የመገናኛ ብዙኃን ባለፈው ሰኞ ዘገባዎቻቸው የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር በዚህ ሳምንት ወደ ካይሮ በማቅናት ከግብፅ አቻቸው ከፊልድ ማርሻል አብዱልፋታህ አል ሲሲ ጋር በሁለቱ አገሮች የጋራ የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ወደ ግብፅ በዚህ ሳምንት እንደሚያመሩ የሱዳን ትሪቡን ዘገባ ያመለክታል፡፡ የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ባለፈው ሰኞ በሰጡት መግለጫ ደግሞ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ማቆም እንደሚገባት ተናግረዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ የኃይል ማመንጫ ግድብ መገንባት ከፈለገች መጠኑ አነስተኛ መሆን ይገባዋል፤›› ብለዋል፡፡ እንደሳቸው አባባል የህዳሴው ግድብ ግንባታ ከታቀደው ስድስት ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ወደ 30 በመቶ ዝቅ ማለት አለበት፡፡ በዚህ ስሌት የታላቁ የህዳሴ ግድብ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ወደ 1,800 ሜጋ ዋት መውረድ አለበት፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ 45 አባላትን የያዘ የግብፅ የዲፕሎማሲ ቡድን ከጥር 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ለአምስት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ግብፅ በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ተቃውሞ ለአፍሪካ ኅብረት እንደሚያሳውቅና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትንም እንደሚያነጋግር ለመረዳት ተችሏል፡፡ኢትዮጵያን የሚጐበኘው የልዑካን ቡድን በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማሲ ኢንስቲትዩት ኃላፊ አምባሳደር ዓሊ ኣል ሃዲዴ የሚመራ መሆኑን በኢትዮጵያ የግብፅ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡ የልዑካን ቡድኑ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ኃላፊና ከኅብረቱ የመሠረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽነር ጋር እንደሚመክር የተያዘው ፕሮግራም ያስረዳል፡፡ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ ከዓባይ ተፋሰስ ዳይሬክቶሬትና ከሕግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ኃላፊዎች ጋር እንደሚነጋገር ታውቋል፡፡ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በመገናኘት በህዳሴው ግድብ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በቅርቡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ፣ ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር የወገነችው ለራሷ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በአጋጣሚ ለድርድር በካርቱም በቆዩባቸው ጊዜያት በተለያዩ መስጊዶች ውስጥ ሳይቀር የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሱዳንን እንዴት ሊጠቅም እንደሚችል ሲሰበክ በግርምት መታዘባቸውን በመግለጽ፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጐን ለራሷ ጥቅም ስትል መቆሟን መረዳት ይቻላል ብለዋል፡፡የግብፅ ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ጋር በሚደረገው ውይይትም ሆነ ድርድር ሱዳን የግብፅን ጥቅም የሚፃረር አቋም እንድትይዝ አለመፈለጋቸው ቢነገርም፣ ሱዳን እስካሁን የግድቡን ግንባታ እንደምትደግፍ ነው የሚታወቀው፡፡ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን ለመሰለፍ የቻለችው በሦስቱ አገሮች ተወክሎ ሲሠራ የነበረውና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ያካተተው የኤክስፐርቶች ፓነል ሪፖርት ድምዳሜን አገናዝባ ነው፡፡ በሪፖርቱ ግድቡ በሱዳንም ሆነ በግብፅ ላይ ይህ ነው የሚባል ጉዳት እንደማያደርስ ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ምንም እንኳ የግብፅ ባለሥልጣን የሱዳን አቋም ከኢትዮጵያ ጋር ወግኗል መባሉን ተባራሪ ወሬ ነው ቢሉም፣ የሱዳን ባለሥልጣናት በአደባባይ ድጋፋቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ (ሪፖርተር)
5ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/24864/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
84d1a64003381490b114fddb6e6e17f2
dab156d5330e184aed7b9e7c22d58b35
ሳውዲ አረብያ በሰሜን የሚያዋስኑዋት የትኞቹ ሀገራት ናቸው?
ሳዑዲ አረቢያ የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡ አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡
null
null
https://huggingface.co/datasets/israel/AmharicQA
771fffa685a9b3a9a5173b0c4ce0c141
979192fa269abf16c9550501401b48d3
ከሁለት ሳምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሰር የዋሉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የጠየቀው ተጨማሪ ቀን ፍርድ ቤት ተፈቅዶለታል።
ፍርድ ቤት ለፖሊስ በአቶ እስክንድር ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ\nዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ እስክንድር ነጋ የብሔርና የሐይማኖት ግጭት እንዲፈጠር ወጣቶችን በማደራጀት ገንዘብና የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ጠበቃቸው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው ውድመት በንብረት ላይ እንዲሁም በሰዎች ህይወትና በአካል ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል የሚል ክስ በፖሊስ መቅረቡን ጠበቃው ጠቅሰዋል። ጉዳያቸው በፌደራል የመጀመሪያ አራዳ ምድብ ችሎት የሚታይ ቢሆንም ለደህንነት ሲባል ችሎቱ ልደታ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንደተሰየመ የተናገሩት አቶ ሄኖክ፤ ፖሊስ ሃያ ምስክሮችን ማድመጡን እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃዎችን እየተመረመረ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ እስካሁን ያከናወናቸውን መረጃ የማሰባሰብና ምርመራ የማካሄድ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አመልክቶ ቀሩኝ የሚላቸው ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከዚህ ሌላ አቶ እስክንድር ለፍርድ ቤቱ ተፈጽሞብኛል ያሉትን በደል ያቀረቡ ሲሆን፤ ይህም በቁጥጥር ሰር በዋሉበት ዕለት በፌደራል ፖሊስ አባላት ድብደባ እንደተፈጻመባቸው እራሳቸውና ጠበቃቸው ለችሎቱ አቤት ብለዋል። ፍርድ ቤቱም በቀረበው አቤቱታ መሰረት በአቶ አስክንድር ላይ ድብደባ የፈጸሙት የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ምርመራ እንዲካሄድና እንዲጣራ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄን በተመለከተ የአቶ አስክንድር ጠበቆች ፖሊስ ማስረጃ እንዳለው ለችሎቱ መግለጹንና ጠቅላይ አቃቤ ህግም ተከሳሹን ወንጀለኛ የሚያስብላቸው ማስረጃ ማግኘቱን ማመልከታቸው አስረድተዋል። ስለዚህም እነዚህ ማስረጃዎች ደግሞ በፖሊስ እጅ መኖራቸውን በመጥቀስ ተጨማሪ የጊዜ ገደብ መጠየቅ ተገቢ አይደለም ብለው ለፍርድ ቤቱ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ፍርድ ቤቱ በቀረበው ተቃውሞ ላይ በሰጠው ምላሽ ምንም እንኳን ፖሊስ ማስረጃ አግኝቻለሁ ቢልም ምርመራው አልቋል ብሎ ስለማያምን ተጨማሪ 13 የምርመራ ቀናት መስጠቱ አስፈላጊ ነው በማለት ለሐምሌ 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ጠበቆች ግን መረጃዎች በፖሊስ እጅ ያሉ በመሆናቸው ምርመራውን በራሱ ለማካሄድ የሚችል በመሆኑ ተጨማሪ ቀን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለው ቢከራከሩም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል ሲሉ አቶ ሄኖክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ እስክንድር ነጋ ጠበቃ ጨምረው እንደተናገሩት ደንበኛቸው ቀደም ሲል ታስረውበት ከነበረው የማረፊያ ቦታ ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወራቸውንም ለቢቢሲ ገልጸዋል።
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
82508192c80448ebe169b9f7bde789e2
3a2d62b61692c53e9a3c88c1fb906c3a
ስለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እስካሁን የምናውቀው
ስለአርቲስቱ ግድያ እና ከግድያው ጋር ተያይዘው ስለተከሰቱ ነገሮች የእስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። የሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመቶ የመገደል ዜና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መዘዋወር የጀመረው ከምሽት 5፡30 አካባቢ ጀምሮ ነበር። በርካቶች የታዋቂውን ድምጻዊ ግድያን በማስመልከት ሃዘናቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲገልጹ ነበር። ከዚያም ከእኩለ ለሊት በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው አርቲስት ሃጫሉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ከምሽቱ 3፡30 አከባቢ በጥይት ተመቶ መገደሉን አረጋገጡ። ኮሚሽነሩ ጨምረውም በግድያው ወንጀል የተጠረጠሩ የተወሰኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። ከእኩለ ለሊት በኋላ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ሰዎች ሃዘናቸውን ለመግለጽ ወደ መንገድ ወጡ። ሌሊቱን በፌስቡክ አማካኝነት ሲሰራጩ በነበሩ የቀጥታ ስርጭቶች፤ በርካቶች መንገድ ላይ በመውጣት ሲያለቅሱ ታይተዋል። በምሥራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞችም ንጋት ላይ መንገድ ዝግ የተደረገባቸው ከተሞች ነበሩ። የአስከሬን ሽኝት ከአዲስ አበባ የሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬን ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ እንደተሸኘ የተነገረ ሲሆን። ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ የአርቲስቱን አስከሬን ለመሸኘት ወጥቷል። አስከሬን ለመሸኘት የወጡ ሰዎች ሃዘናቸውን በተለያየ መልክ ሲገልጹ ነበር። በዚህ ጊዜ ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ ሲተኩስ በስፍራው የነበሩ ሰዎች በፌስቡክ የቀጥታ ካሰራጩት ምስል ላይ ታይቷል። በተጨማሪም የድምጻዊውን አስክሬን ለመሸኘት ከወጡ ሰዎችም ቢቢሲ አረጋግጧል። የአስከሬን አቀባበል በአምቦ ዛሬ ንጋት ላይ የአርቲስት ሃጫሉ አስከሬን በበርካታ አድናቂዎቹ ታጅቦ ወደ አምቦ ሲያመራ የነበረ ቢሆንም ቀብሩ መፈፀም ያለበት አዲስ አበባ ነው የሚሉ ተቃውሞዎች መሰማታቸውን ተከትሎ አስክሬኑ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጎ ነበር። ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰም በኋላ አስክሬኑ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማዕከል እንዲያረፍ ተደርጎ ቆይቷል። ከዚያም አስክሬኑ ወደ አምቦ በሄሊኮፕተር ተጭኖ ወደ ከአምቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ወደ ሚገኘው ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ መወሰዱ ተነግሯል። ማለዳ አምቦ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ አስክሬኑን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ነበር። “የከተማው ሕዝብ ወደ ዋና መንገድ ወጥቷል። ከገጠርም በጣም ብዙ ሰዎች በፈረስ እየመጡ ነው” ሲሉ አንድ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችም በነዳጅ ማደያ እና ባንክ ቤቶች በመሳሰሉት ተቋማት አካባቢ እንጂ በብዛት በከተማዋ ውስጥ እንደማይታዩ አኚሁ ነዋሪ ጨምረው ተናግረው ነበር። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ስነስርዓት መቼ እንደሚፈፀም ከቤተሰቡም ሆነ ከመንግሥት አካል እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም። ሃጫሉ ከዚህ ቀደም ምን ብሎ ነበር? ሃጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ ቀደም ቢቢሲን ጨምሮ ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻዎች ይደርሰው እንደነበረ ተናግሯል። ከሳምንት በፊት ሰኔ 15/2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ በተላለፈው ቃለ መጠይቁ፤ ሃጫሉ “እየታገልኩ እኮ ነው የምኖረው” በማለት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ እንደሚደርስበት ተናግሯል። የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ማን ምን አለ? ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በድምጻዊው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን "ውድ ህይወት አጥተናል" በማለት "የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሃዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ...
null
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
607d3620e4ec91a905c23dbefa26d01f
2ac0d6046042faf6d243e67b79673bb2
የኢትዮጵያ መርከቦች ለኢትዮጵያ ነዳጅ እየጫኑ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ መስከረም 10/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ባሕር ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፤ ነገር ግን ለሜቴክ በዱቤ የሰጠው የ2 ቢሊዮን ብር ዱቤ አገልግሎት እንዳልተከፈለው ገልጿል፡፡የኢትዮጵያ ባሕር ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ባለፈው የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ እንዳስታወቁት ባለፈው ዓመት አማካይ የኮንቲነር የወደብ ቆይታ 6 ቀን ከ6 ሰዓት ነበር፡፡
0ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.amharaweb.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%88%98%e1%88%ad%e1%8a%a8%e1%89%a6%e1%89%bd-%e1%88%88%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%90%e1%8b%b3%e1%8c%85-%e1%8a%a5/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
5687fc98d278c3b98a63b61af7c52665
5334dfc08ca4088747be23a3e55e9b91
ኦሮማይ
ኦሮማይ በጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ በ1975 ዓ.ም ለኅትመት የበቃ ድርሰት ነው። የመጽሐፉ መቼት በጊዜው የኢትዮጲያ ኣካል በነበረው በኤርትራ በረሐዎች ይካሄድ በነበረውቀይ ኮከብ ዘመቻ ዙርያ የሚያጠነጥን ነው። ምስጋና በዓሉ ግርማ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ደርግ
null
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
d2037e648dbb4a0e6e45c50f4231d54d
3a2d5a12613dfd09bfd1fb00db26eea8
በከፍተኛ ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ለገጣፎ እና ገላን አቻ ተለያይተዋል
የ2013 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ ባቱ ላይ 4:00 በተደረገ የምድብ ሀ ጨዋታ ሲጀመር ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ገላን ከተማ ያለ ጎል ተለያይተዋል።የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ኢብራሂም መሐመድ እና ኢንጅነር ኤሌሮ አፒዮ በክብር እንግድነት በመገኘት ያስጀመሩት ጨዋታ ቀዝቀዝ ባለ ፉክክር፣ ጥቂት የግብ ዕድል እና ጥሩ ዳኝነት ታጅቦ ተከናውኗል።የመጀመርያው አርባ አምስት አጋማሽ ደቂቃ ድረስ ይህ ነው የሚባል የግብ ሙከራ ያላሳየው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እንቅስቃሴ በሜዳው አጋማሽ ላይ ተገድቦ የቆየ ሲሆን በ26ኛው ደቂቃ ላይ ለገጣፎዎች በቅጣት ምት እና በ28ኛው ደቂቃ ዘካርያስ ከበደ አሻምቶት አንዋር አብዱልቃድር በሞከረው ኳስ ለግብ ቀርበው ነበር። በገላኖች በኩል በ30ኛው ደቂቃ ቢንያም ካሳሁን በግል ጥረቱ ከመስመር እየገፋ ሄዶ የሞከረው ሙከራ ተጠቃሽ ነበር።ጨዋታው ቀስ በቀስ እየተሟሟቀ ቀጥሎ የተሻለ ፉክክር አስተናግዷል። በ32ኛው ደቂቃ የገላን ተከላካዮች የሰሩትን የቅብብል ስህተት ተጠቅሞ ጥሩ ኳስ ያገኘው አንዋር አክርሮ መትቶ ግብ ለማስቆጠር ቢጥርም ኳስ እና መረብን ማገናኘት አልቻለም። አብዱለጢፍ ሙራድ እና ዝናቡ ባፋ በ43ኛው እና በ45ኛው ደቂቃ ከተመሳሳይ ቦታ ለማስቆጠር ሞክረው መክኖባቸዋል። የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ በጭማሪው ሰዓት ገላኖች ጥሩ እድል አግኝተው አብዱልለጢፍ ሙራድ ከመስመር አፍትልኮ ወደ ጎል በሚያመራበት ወቅት የለገጣፎ ግብ ጠባቂ አብርሀም ከተማ በመውጣት በሰራው ጥፋት በእለቱ ዳኛ አሸናፊ በላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዶል። ይህም የውድድሩ የመጀመርያ ቀይ ካርድ ሆኖ ተመዝግቧል።ከመጀመሪያው አጋማሽ በተቃራኒ መልኩ የጀመረው ሁለተኛው አጋማሽ ሙከራ ለማስተናገድ 3 ደቂቃዎች ብቻ ፈጅተውበታል። በ48ኛው ደቂቃ ተደራጅተው ወደ ገላኖች የግብ ክልል የደረሱት ጣፎዎች በፋሲል አስማማው አማካኝነት ግብ ቢስቆጥሩም ከጨዋታ ውጭ ተብሎባቸዋል። ለገጣፎዎች ምንም እንኳን ወደ ራሳቸው የግብ ክልል ተጠግተው ቢከላከሉም በአንድ አንድ አጋጣሚዎች ፍጥነት የታከለበት ሽግግር በማድረግ ግብ ለማስቆጠር ጥረዋል። በዚህም በ63ኛው ደቂቃ ገላኖች ትተውት የሄዱትን ክፍተት በመጠቀም በመልሶ ማጥቃት ጥሩ ሙከራ ሳዲቅ ተማም እና ፋሲል አስማማው አድርገው መክኖባቸዋል።በተሻለ ኳሱን ተቆጣጥረው ለመጫወት ጥረት ያደረጉት ገላኖች በበኩላቸው በ75፣ 81 እና 87ኛው ደቂቃ ከመስመር ባሻሟቸው ኳሶች ጥሩ ጥሩ እድል ቢፈጥሩም ግብ ሳያስቆጥሩ ቀርተዋል። የ2013 የመጀመሪያ ጨዋታም በዚህ መልኩ ያለ ግብ ተጠናቋል።
2ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/63013
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
End of preview. Expand in Data Studio
Downloads last month
6